ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 2:12-14

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 2:12-14 አማ2000

እኛ የዚ​ህን ዓለም መን​ፈስ የተ​ቀ​በ​ልን አይ​ደ​ለም፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሰ​ጠ​ንን ጸጋ እና​ውቅ ዘንድ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሆ​ነ​ውን መን​ፈስ ተቀ​በ​ልን። ይህም ትም​ህ​ር​ታ​ችን ከሰው የተ​ገኘ ትም​ህ​ርት አይ​ደ​ለም፤ የአ​ነ​ጋ​ገር ጥበ​ብም አይ​ደ​ለም፤ መን​ፈስ ቅዱስ የገ​ለ​ጸው ትም​ህ​ርት ነው እንጂ፤ መን​ፈ​ሳዊ ጥበ​ብም ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ የሚ​ሆ​ነ​ውን መር​ም​ረው ለሚ​ያ​ውቁ ለመ​ን​ፈ​ሳ​ው​ያን ነው። ለሥ​ጋዊ ሰው ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ ነገር ሞኝ​ነት ይመ​ስ​ለ​ዋ​ልና፥ አይ​ቀ​በ​ለ​ውም፤ በመ​ን​ፈ​ስም የሚ​መ​ረ​መር ስለ​ሆነ ሊያ​ውቅ አይ​ች​ልም።