ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 15:17-22

ወደ ቆሮ​ን​ቶስ ሰዎች 1 15:17-22 አማ2000

ክር​ስ​ቶ​ስም ከሙ​ታን ካል​ተ​ነሣ ማመ​ና​ችሁ ከንቱ ነው፤ ገናም በኀ​ጢ​አ​ታ​ችሁ አላ​ችሁ። እን​ግ​ዲ​ያስ በክ​ር​ስ​ቶስ አም​ነው የሞቱ ጠፍ​ተ​ዋላ። በዚህ ዓለም ሕይ​ወት ብቻ ክር​ስ​ቶ​ስን ተስፋ ከአ​ደ​ረ​ግ​ነው ከሰው ሁሉ ይልቅ ጉዳ​ተ​ኞች ነን። አሁ​ንም ክር​ስ​ቶስ ከሞቱ ሰዎች ሁሉ አስ​ቀ​ድሞ ተነ​ሥ​ቶ​አል። በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ሰው ሞት መጥ​ቶ​አ​ልና፤ በሁ​ለ​ተ​ኛው ሰው ትን​ሣኤ ሙታን ሆነ። ሁሉ በአ​ዳም እን​ደ​ሚ​ሞት እን​ዲሁ በክ​ር​ስ​ቶስ ሁሉ ሕያ​ዋን ይሆ​ናሉ።