መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 9
9
1እስራኤልም ሁሉ ስለ ኀጢአታቸው ወደ ባቢሎን ከተማረኩ በኋላ፥ በየትውልዳቸው ተቈጠሩ፤ እነሆም በእስራኤልና በይሁዳ ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፈዋል። 2በእስራኤል ከተሞችና በአውራጃዎቻቸው መጀመሪያ የተቀመጡ ካህናት፥ ሌዋውያንም፥ አገልጋዮችም#ዕብ. “ናታኒምም” ይላል። ነበሩ። 3ከይሁዳ ልጆችና ከብንያም ልጆች፥ ከኤፍሬምና ከምናሴ ልጆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። 4ከይሁዳ ልጅ ከፋሬስ ልጆች የባኔ ልጅ የአምሪ ልጅ #“የባኔ ልጅ የአምሪ ልጅ” የሚለው በግሪክ ሰባ. ሊ. የለም። የዖምሪ ልጅ የዓሚሁድ ልጅ ዑታይ ደግሞ ተቀመጠ። 5ከሴሎናውያንም በኵሩ ዓሣያና ልጆቹ። 6ከዛራም ልጆች ኢያሄልና ወንድሞቻቸው፥ ስድስት መቶ ዘጠና። 7ከብንያምም ልጆች የሐስኑአ ልጅ የሆዳይዋ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሎ፤ 8የይሮሐም ልጅ ኢያብናአ፤ የሚክሪ ልጅ የኦዚ ልጅ ኤላ፤ የበንያስ ልጅ የራጉኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ ሜሱላም፤ 9በየትውልዳቸውም ወንድሞቻቸው ዘጠኝ መቶ አምሳ ስድስት ነበሩ፤ እነዚህ ሰዎች ሁሉ የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች ነበሩ።
10ከካህናቱም ዮዳኤ፥ ዮአሪብ፥ ያኪን፤ 11የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ፥ የመራዩት ልጅ፥ የሳዶቅ ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ የኬልቅያስ ልጅ ዓዛርያስ፤ 12የመልክያ ልጅ፥ የጳስኮር ልጅ፥ የይሮሐም ልጅ፥ አዳያ፤ የኤሜር ልጅ የምስልሞት ልጅ፥ የሜሱላም ልጅ፥ የኤሕዜራ ልጅ፥ የዓዴኤል ልጅ መዕሣይ፤ 13የአባቶቻቸውም ቤቶች አለቆች ወንድሞቻቸው ሺህ ሰባት መቶ ስድሳ ነበሩ፤ ለእግዚአብሔር ቤትም ማገልገል ሥራ እጅግ ብቁዎች ሰዎች ነበሩ።
14ከሌዋውያንም ልጆች ከሜራሪ ልጆች የአሳብያ ልጅ፥ የዓዝሪቃም ልጅ፥ የአሱብ ልጅ ሸማያ፤ 15በቀባቃር፥ ኤሬስ፥ ጋላል፥ የአሳፍ ልጅ የዝክሪ ልጅ የሜካ ልጅ ማታንያስ፤ የኤዶታም ልጅ የጋላል ልጅ የሰማያ ልጅ አብድያ፤ 16በነጦፋውያንም መንደሮች የተቀመጠው የሕልቃና ልጅ የአሳ ልጅ በራክያ።
17በረኞችም ሰሎም፥ ዓቁብ፥ ጤልሞን፥ አሒማን፥ ወንድሞቻቸውም ነበሩ፤ ሰሎምም አለቃ ነበረ። 18እስከዛሬም ድረስ በንጉሥ በር በምሥራቅ በኩል ነበሩ፤ ለሌዊ ልጆች ሰፈር በረኞች ነበሩ። 19የቆሬም ልጅ የአብያሳፍ ልጅ የቆሬ ልጅ ሰሎም ከአባቱ ቤት የነበሩ ወንድሞቹ ቆሬያውያን በማገልገል ሥራ ላይ ነበሩ፤ የድንኳኑንም መድረክ ይጠብቁ ነበር። አባቶቻቸውም የእግዚአብሔርን ሰፈር መግቢያ ይጠብቁ ነበር። 20አስቀድሞም የአልዓዛር ልጅ ፊንሐስ አለቃቸው ነበረ። እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረ። 21የሜሱላም ልጅ ዘካርያስ የምስክሩ ድንኳን ደጅ በረኛ ነበረ። 22የመድረኩ በረኞች ይሆኑ ዘንድ የተመረጡ እነዚህ ሁሉ ሁለት መቶ ዐሥራ ሁለት ነበሩ። እነዚህ በመንደሮቻቸው በየትውልዳቸው ተቈጠሩ። ዳዊትና ነቢዩ ሳሙኤል ታማኝነታቸውን አይተው በሥራቸው አቆሙአቸው። 23እነርሱና ልጆቻቸውም በእግዚአብሔር ቤት በድንኳኑ ደጆች ላይ በረኞች ነበሩ። 24በአራቱ ማዕዘኖች፥ በምሥራቅ፥ በምዕራብ፥ በሰሜን፥ በደቡብ በሮች ነበሩ። 25ወንድሞቻቸውም በመንደሮቻቸው ሆነው፥ በየሰባቱ ቀን ከእነርሱ ጋር ሊሆኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ ይገቡ ነበር። 26እነዚህ አራቱ ኀያላን ሰዎች ለአራቱ በሮች ኀላፊዎች ነበሩ። ሌዋውያንም በእግዚአብሔር ቤት ባሉ ጓዳዎችና ቤተ መዛግብት ላይ የተሾሙ ነበሩ። 27የእግዚአብሔርንም ቤት መክፈቻ የሚይዙ፥ ጥዋት ጥዋትም ደጆቹን የሚከፍቱ እነርሱ ነበሩና።
28ዕቃውንም በቍጥር ያገቡና ያወጡ ነበርና ከእነዚህ አንዳንዶቹ በማገልገያው ዕቃ ላይ ሹሞች ነበሩ። 29ከእነርሱ አንዳንዶቹ በአገልግሎቱ ዕቃዎች በመቅደሱ ዕቃ ሁሉ፥ በመልካሙም ዱቄት፥ በወይን ጠጁም፥ በዘይቱም፥ በዕጣኑም፥ በሽቱውም ላይ ሹሞች ነበሩ። 30ከካህናቱም ልጆች አንዳንዶቹ ዕጣኑንና የሽቱውን ቅባት ያዘጋጁ ነበር። 31የቆሬያዊውም የሰሎም በኵር ሌዋዊው ማቲትያ ለታላቁ ሊቀ ካህናት#“ለታላቁ ሊቀ ካህናት” የሚለው በዕብ. የለም። በምጣድ በሚጋገረው ነገር ላይ ሹም ነበረ። 32በየሰንበቱም ያዘጋጁ ዘንድ ቀዓታዊው በንያስና ወንድሞቻቸው በገጹ ኅብስት ላይ ሹሞች ነበሩ።
33ከሌዋውያንም ወገን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች የነበሩ መዘምራን በየሰሞናቸው አገልጋዮችና ሹሞች ነበሩ፤ ሥራቸውም ሌሊትና ቀን ነበረ። 34እነዚህ ከሌዋውያን የአባቶቻቸው ቤቶች አለቆች በየትውልዳቸው አለቆች ነበሩ። እነዚህም በኢየሩሳሌም ይቀመጡ ነበር።
35የሚስቱ ስም መዓካ የነበረው የገባዖን አባት ይዒኤል በገባዖን ይቀመጥ ነበረ። 36የበኵር ልጁም ስም ዓብዶን፥ሁለተኛው ሲር፥ ሦስተኛው ቂስ፥ አራተኛው በኣል፥ አምስተኛው ኔር፥ ስድስተኛውም ናዳብ፤ 37ሰባተኛው ግዱር፥ ወንድሙ#ዕብ. “አሒዩ” ይላል። ዘካርያስም፥ ሜቅሎትም። 38ሜቅሎትም ሳምአን ወለደ፤ እነርሱም ደግሞ ከወንድሞቻቸው ጋር በኢየሩሳሌም በወንድሞቻቸው መካከል ይቀመጡ ነበር። 39ኔርም ቂስን ወለደ፤ ቂስም ሳኦልን ወለደ፤ ሳኦልም ዮናታንን፥ ሜልኪሳን፥ አሚናዳብን፥ አስበኣልን ወለደ። 40የዮናታንም ልጅ መሪበኣል ነበረ፤ መሪበኣልም ሚካን ወለደ። 41የሚካም ልጆች ፒቶን፥ ሜሌክ፥ ታራ፥ አካዝ ነበሩ፤ 42አካዝም ኢያዳዕን ወለደ፤ ኢያዳዕም ጋሌሜትን፥ ጋዝሞትን፥ ዘምሪን ወለደ፤ ዘምሪም ማሳዕን ወለደ። 43ማሳዕም በዓናን ወለደ፥ ልጁ ረፋያ ነበረ፥ ልጁ ኤልዓሣ፥ ልጁ ኤሴል፤ 44ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ ቦኬርዩ፥ እስማኤል፥ ሰዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ የኤሴል ልጆች ነበሩ።#ምዕ. 8 ቍ. 38 የወረደውን ተመልከት።
Currently Selected:
መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 9: አማ2000
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ