ትንቢተ ዘካርያስ 3
3
ነቢያዊ ራእይ፦ ሊቀ ካህኑ ኢያሱ
1 #
ኢዩ. 1፥6—2፥7፤ 1ዜ.መ. 21፥1። ከዚያም እርሱ ታላቁን ካህን ኢያሱን በጌታ መልአክ ፊት ቆሞ አሳየኝ፥ ሰይጣንም እርሱን ለመክሰስ በስተ ቀኙ ቆሞ ነበር። 2#ይሁዳ 1፥9፤ አሞጽ 4፥11።ጌታም ሰይጣንን፦ “ሰይጣን ሆይ፥ ጌታ ይገሥጽህ፤ ኢየሩሳሌምን የመረጠ ጌታ ይገሥጽህ! በውኑ ይህ ከእሳት የተነጠቀ ትንታግ አይደለምን?” አለው።
3ኢያሱም እድፋም ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር። 4#ሉቃ. 15፥22፤ ራእ. 19፥8፤ ኢሳ. 6፥7፤ ኤር. 31፥34፤ ሕዝ. 36፥33።መልአኩም መልሶ በፊቱ የቆሙትን፦ “እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ” አላቸው። እርሱንም፦ “እነሆ፥ አበሳህን ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ” አለው። 5ከዚያም፥ “ንጹሕ የራስ ላይ ጥምጣም ያድርጉለት” አለ። እነርሱም በራሱ ላይ ንጹሕ ጥምጥም አደረጉ፥ ልብስንም አለበሱት፤ የጌታም መልአክ በአጠገቡ ቆሞ ነበር። 6የጌታም መልአክ በኢያሱ ላይ እንዲህ ሲል ብያኔ ሰጠ፦ 7“የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ በመንገዴ ብትሄድ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፥ በቤቴ ላይ ትፈርዳለህ፥ አደባባዮቼንም ትጠብቃለህ፤ እኔም በዚህ ስፍራ ከቆሙት ጋር ስፍራን እሰጥሃለሁ።”
ተጨማሪ ትንቢት
8 #
ኢሳ. 8፥18። ሊቀ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ! በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ ለሚመጣው ነገር ምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ! እነሆ፥ እኔ አገልጋዬን ቁጥቋጡን አወጣለሁ። 9#ዘካ. 4፥7፤ 10፤ ኢሳ. 28፥16፤ ራእ. 5፥6።በኢያሱ ፊት ያኖርሁትን ድንጋይ ተመልከት፤ በአንዱ ድንጋይ ላይ ሰባት ዐይኖች አሉ፤ እነሆ፥ ቅርጹን እቀርጻለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ የዚያችንም ምድር በደል በአንድ ቀን አስወግዳለሁ። 10#1ነገ. 5፥5፤ ሚክ. 4፥4።በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ እያንዳንዱ በወይኑና በበለሱ ስር ሆኖ ባልንጀራውን ይጠራል።
Currently Selected:
ትንቢተ ዘካርያስ 3: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ