የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

ትንቢተ ዘካርያስ 13

13
ስለ ሐሰት ራእይ ፍጻሜ ትንቢት
1 # ሕዝ. 36፥25፤ 47፥1፤ ዮሐ. 7፥38። በዚያ ቀን ለዳዊት ቤትና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ከኃጢአትና ከርኩሰት የሚያነጻ ምንጭ ይፈልቃል። 2በዚያ ቀን፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፥ የጣዖታትን ስም ከምድር አጠፋለሁ፥ ከዚያም በኋላ አይታሰቡም፤ ደግሞም ሐሰተኞችን ነቢያትና ርኩስ መንፈስን ከምድር ላይ አስወግዳለሁ። 3#ዮሐ. 19፥34።አሁንም ቢሆን ማንም ትንቢት ቢናገር የወለዱት አባቱና እናቱ፦ “አንተ በጌታ ስም ሐሰትን ተናግረሃልና በሕይወት አትኖርም” ይሉታል። ትንቢትንም ሲናገር የወለዱት አባትና እናቱ ይወጉታል።
4 # 2ነገ. 1፥8፤ ማቴ. 3፥4። በዚያም ቀን እያንዳንዱ ነቢይ ስለሚናገረው ትንቢት ስለ ራእዩ ያፍራል፥ ለማታለልም የማቅ ልብስ አይለብሱም። 5#አሞጽ 7፥14።ነገር ግን እያንዳንዱ፦ “ከታናሽነቴ ጀምሮ አገልጋይ ነበርኩ፥ መሬት አራሽ ነኝ እንጂ ነቢይ አይደለሁም” ይላል። 6#1ነገ. 18፥28።ማንም ሰው፦ “ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቁስል ምንድነው?” ብሎ ቢጠይቀው፥ እያንዳንዱም፦ “በወዳጆቼ ቤት የቈሰልኩት ቁስል ነው” ይላል።
ስለ ሰይፍ መዝሙር
7 # ሕዝ. 34፥1-8፤ ማቴ. 26፥31። ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ። 8በምድርም ሁሉ ላይ ሁለት ሦስተኛው ተቈርጠው ይጠፋሉ፥ ይላል ጌታ፤ አንድ ሦስተኛው ክፍልም በእርሷ ይቀራል። 9#ኢሳ. 1፥25፤ 48፥10፤ መዝ. 91፥15፤ ኢሳ. 65፥24፤ ዘካ. 8፥8፤ ኤር. 31፥31።አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ