መጽሐፈ ጦቢት መግቢያ
መግቢያ
በነነዌ የሚኖር ጦቢት በመባል የሚታወቅ አንድ ሰው ነበር። እርሱም ከወገኖቹ ከንፍታሌም ነገድ ጋር ተማርኮ ነበር፤ ጦቢት ለእግዚአብሔር ያደረና ሕግ አክባሪ ሲሆን ከጊዜ በኋላ ዓይነ ስውር ሆነ። እንደ መጽሐፈ ጦቢት አቀራረብ በንጉሥ ሰሎሞን ሞት ምክንያት መንግሥቱ ሲከፋፈል ጦቢት ወጣት ነበረ። ዘመኑም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ 931 ነበር። ጦቢት እስከ ነነዌ ውድቀት ድረስ ልጁ አልሞተም ነበር። ይህም ቅድመ ልደተ ክርስቶስ 612 ዓመት ላይ ነበር። የስልምናሶር ቀጥተኛው ወራሽ ስናክሪም እንደ ነበረ መጽሐፈ ጦቢት ይገልጻል። ስለ ሳርጐን መንግሥት ግን የገለጠው ምንም ነገር የለም።
ጦቢት ኤቅባጥና በሚባል ቦታ የሚኖር ራጉኤል የሚባል ዘመድ ነበረው። የዚህም ሰው ሴት ልጅ ሣራ ለሰባት ወንዶች የተዳረች ቢሆንም ሰባቱም ሙሽሮች በየሰርጉ ማግስት አስማድዮስ በተባለው ጋኔን ተገድለውባታል።
ጦቢትም ሆነ ሣራ ተስፋ ቆርጠው ሞትን ቢመኙም እግዚአብሔር ራሱ በፈቀደው መንገድ መልአኩን ሩፋኤልን በመላክ ለጸሎታቸው መልስ ሰጠ። በአንድ በኩል መልአኩ ሩፋኤል የጦቢትን ልጅ ጦብያን ወደ ራጉኤል በደኀና ወስዶ ከሣራ ጋር እንዲገናኙ ምክንያት ሆነ፤ በተለይም በሰርግ ማግስት የተለመደው የሙሽራ አደጋ እንዳይደርስ ጦቢያ ምን ማድረግ እንዳለበት አስተማረው። በሌላ በኩል ጦቢት ከዓይነ ስውርነት የሚድንበትን መድኃኒት መልአኩ ሩፋኤል ለጦቢያ ሰጠ።
መጽሐፈ ጦቢት ምጽዋት መስጠትን እና በሙታን ስም መልካም ተግባርን መፈጸምን ያስተምራል። በተጨማሪም ስለ መልካም ቤተሰብ ሕይወትና ስለ ጋብቻ ክቡርነት ጠንካራ መልእክት ያስተላልፋል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
የጦቢት ስቃይ (1፥1—3፥6)
የሣራ ችግር (3፥7-17)
ለጉዞ ዝግጅት (4፥1—6፥1)
የጦቢያ ወደ ሚዲያ ጉዞ (6፥2-18)
የሣራ ጋብቻ እና ፈውስ (7፥1—9፥6)
የጦቢያ ወደ ነነዌ የመመለስ ጉዞ እና የጦቢትን ፈውስ (10፥1—11፥18)
ሩፋኤል ማንነቱን እንደ ገለጠ (12፥1-21)
የጦቢት የምስጋና መዝሙር (13፥1-18)
የመዝጊያ ንግግር (14፥1-15)
ምዕራፍ
Currently Selected:
መጽሐፈ ጦቢት መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ