ወደ ሮሜ ሰዎች 11:29-32

ወደ ሮሜ ሰዎች 11:29-32 መቅካእኤ

እግዚአብሔር በጸጋው ስጦታና በመጥራቱ አይጸጸትምና። እናንተም ቀድሞ ለእግዚአብሔር እንዳልታዘዛችሁ፥ አሁን ግን በማይታዘዙት ምክንያት ምሕረት እንዳገኛችሁ፥ እንዲሁም እናንተ ያገኛችሁትን ምሕረት፥ እነርሱ ደግሞ ምሕረትን እንዲያገኙ፥ እነዚህ ደግሞ አሁን አልታዘዙም። እግዚአብሔር በሁሉም ላይ ምሕረቱን ለማሳየት ሁሉን በአለመታዘዝ ዘግቶታልና።”