የዮሐንስ ራእይ 19:11-14

የዮሐንስ ራእይ 19:11-14 መቅካእኤ

ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም ነጭ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም። ዐይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ናቸው፤ በራሱ ላይም ብዙ ዘውዶች አሉ፤ ከእርሱም በቀር ማንም የማያውቀው የተጻፈ ስም አለው፤ በደምም የተረጨ ልብስ ተጐናጽፎአል፤ ስሙም የእግዚአብሔር ቃል ተብሏል። በሰማይም ያሉት ሠራዊት ነጭና ጥሩ ቀጭን የተልባ እግር ልብስ ለብሰው በነጭ ፈረሶች ላይ ተቀምጠው ይከተሉት ነበር።