የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

የዮሐንስ ራእይ 17

17
ታላቂቱ አመንዝራ ሴትና አውሬው
1 # ኤር. 28፥13። ሰባቱንም ጽዋዎች ከያዙት ከሰባቱ መላእክት አንዱ መጥቶ “ና፤ በብዙም ውሃዎች ላይ የተቀመጠችውን የታላቂቱን አመንዝራ ሴት ፍርድ አሳይሃለሁ፤ 2#ኢሳ. 23፥17፤ ኤር. 28፥7።የምድርም ነገሥታት ከእርሷ ጋር ሴሰኑ፤ በምድርም የሚኖሩ በዝሙትዋ ወይን ጠጅ ሰከሩ፤” ብሎ ተናገረኝ። 3#ራእ. 13፥1።በመንፈስም ወደ በረሓ ወሰደኝ፤ የስድብም ስሞች በሞሉበት፥ ሰባት ራሶችና ዐሥር ቀንዶችም ባሉት በቀይ አውሬ ላይ አንዲት ሴት ተቀምጣ አየሁ። 4#ኤር. 28፥7።ሴቲቱም ሐምራዊና ቀይ ልብስ ለብሳ በወርቅና በከበሩ ድንጋዮች በዕንቈችም ተሸልማ ነበር፤ በእጅዋም የሚያስጸይፍ ነገርና የዝሙትዋ ርኩሰት የሞላባትን የወርቅ ጽዋ ይዛ ነበር 5በግምባርዋም “ታላቂቱ ባቢሎን፥ የአመንዝሮችና የምድር ርኩሰት እናት” የሚል ምስጢራዊ የሆነ ስም ተጻፈ። 6ሴቲቱም በቅዱሳን ደምና በኢየሱስ ምስክሮች ደም ሰክራ አየኋት።
ባየኋትም ጊዜ በእጅጉ ተደነቅሁ። 7መልአኩም እንዲህ አለኝ፦ “ለምንድን ነው የምትደነቀው? የሴቲቱን ምስጢርና የሚሸከማትን፥ ሰባት ራሶችና ዐስር ቀንዶች ያሉትን የአውሬውን ምስጢር እኔ እነግርሃለሁ። 8#ዳን. 7፥7፤ ራእ. 11፥7፤ መዝ. 68፥29።ያየኸው አውሬ አስቀድሞ ነበረ፤ አሁን ግን የለም፤ ከጥልቁም ሊወጣ ነው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል፤ ስሞቻቸውም ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ በሕይወት መጽሐፍ ያልተጻፉ የምድር ኗሪዎች አውሬው አስቀድሞ እንደ ነበረ አሁን ደግሞ እንደሌለ፥ ነገር ግን ተመልሶ እንደሚመጣ ሲያዩ ይደነቃሉ። 9ጥበብ ያለው አእምሮ የሚያስፈልገው እዚህ ላይ ነው። ሰባቱ ራሶች ሴቲቱ የተቀመጠችባቸው ሰባት ተራራዎች ናቸው፤ ሰባትም ነገሥታት ናቸው፤ 10አምስቱ ወድቀዋል፤ አንዱም አለ፤ የቀረውም ገና አልመጣም፤ ሲመጣም፥ ጥቂት ጊዜ ሊቆይ ይገባዋል። 11የነበረውና የሌለውም አውሬ ራሱ ደግሞ ስምንተኛው ነው፤ ከሰባቱም አንዱ ነው፤ ወደ ጥፋትም ይሄዳል። 12#ዳን. 7፥24።ያየሃቸውም ዐሥሩ ቀንዶች ገና ያልነገሡ ዐሥር ነገሥታት ናቸው፤ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት ያህል እንደ ነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ። 13እነዚህ አንድ እቅድ አላቸው፤ ኀይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ። 14እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉት የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ናቸው።”
15እንዲህም አለኝ “አመንዝራይቱ የተቀመጠችባቸው ያየሃቸው ውሃዎች፥ ወገኖችና ብዙ ሰዎች፥ አሕዛብም፥ ቋንቋዎችም ናቸው። 16ያየሃቸውም ዐሥር ቀንዶችና አውሬው አመንዝራይቱን ይጠላሉ፤ ይበዘብዟታል፥ ራቁትዋንም ያደርጓታል፤ ሥጋዋንም ይበላሉ፤ በእሳትም ያቃጥሉአታል። 17የእግዚአብሔርም ቃል እስኪፈጸም ድረስ ዕቅዱን በአንድ ልብ እንዲያደርጉና መንግሥታቸውንም ለአውሬው እንዲሰጡ እግዚአብሔር በልባቸው አሳድሮአልና። 18ያየሃትም ሴት በምድር ነገሥታት ላይ የምትነግሥ ታላቂቱ ከተማ ናት።”

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ