የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 91

91
1በልዑል መጠጊያ የሚኖር
ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል።
2 # መዝ. 18፥3፤ 31፥3-4፤ 42፥10፤ 142፥6፤ 2ሳሙ. 22፥3። ጌታን፦ “አንተ መጠጊያዬና መሸሸጊያዬ ነህ እለዋለሁ”፥
የምታመንበት አምላኬ ነውና።
3እርሱ ከአዳኝ#91፥3 “ከተሰወረ ወጥመድ” የሚሉ ትርጉሞችም አሉ። ወጥመድ
ከሚያስደነግጥም ነገር ያድንሃልና።
4 # መዝ. 17፥8፤ 36፥8፤ 57፥2፤ 63፥8፤ ዘዳ. 32፥11፤ ሩት 2፥12፤ ማቴ. 23፥37። በላባዎቹ ይጋርድሃል፥
ከክንፎቹም በታች ትጠለላለህ፥
ታማኝነቱ እንደ ጋሻና እንደ ቅጥር ይከብብሃል።
5 # ምሳ. 3፥25፤ መኃ. መኃ. 3፥8። ከሌሊት ሽብር፥
በቀን ከሚበርር ፍላጻ፥
6 # ዘዳ. 32፥24። በጨለማ ከሚጓዝ መቅሰፍት፥
በቀትር ከሚደመስስ አደጋ አትፈራም።
7በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም ዐሥር ሺህ ይወድቃሉ፥
ወደ አንተ የሚጠጋ የለም።
8 # መዝ. 92፥12። በዐይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ፥
የኃጥኣንንም ቅጣት ታያለህ።
9ጌታን፥ “አንተ ተስፋዬ ነህ” ብለህ፥
ልዑልን መጠጊያህ አድርገሃልና።
10 # ምሳ. 12፥21፤ ዘዳ. 7፥15። ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥
መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።
11 # ማቴ. 4፥6፤ ሉቃ. 4፥10። በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ
መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፥#ዕብ. 1፥14።
12 # መዝ. 121፥3፤ ምሳ. 3፥23። እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል
በእጆቻቸው ያነሡሃል።
13 # ኢሳ. 11፥8፤ ሉቃ. 10፥19። በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፥
አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
14 # መዝ. 9፥11፤ 119፥132። በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፥
ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ#91፥14 ዕብራይስጡ “ከፍ አደርገዋለሁ” ይላል።
15 # ኢሳ. 43፥2፤ ኤር. 33፥3፤ ዘካ. 13፥9። ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥
በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፥
አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
16 # ምሳ. 3፥2። ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥
ማዳኔንም አሳየዋለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ