የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 85

85
1ለመዘምራን አለቃ፥ የቆሬ ልጆች መዝሙር።
2 # መዝ. 14፥7፤ 126፥4። አቤቱ፥ ምድርህን በመልካም ጎበኘህ፥
የያዕቆብንም ምርኮ መለስህ።
3የሕዝብህን በደል አስቀረህ፥
ኃጢአታቸውንም ሁሉ ይቅር አልክ።
4 # መዝ. 78፥38፤ ዘፀ. 32፥14፤ ኢሳ. 48፥9። መዓትህንም ሁሉ አስወገድህ፥
ከቁጣህ መቅሠፍት ተመለስህ።
5 # መዝ. 80፥4። የመድኃኒታችን አምላክ ሆይ፥ መልሰን፥
ቁጣህንም ከእኛ መልስ።
6 # መዝ. 79፥5፤ 89፥47። በውኑ ለዘለዓለም ትቈጣናለህን?
ቁጣህንስ ለልጅ ልጅ ታስረዝማለህን?
7አቤቱ፥ ሕይወትን ልትሰጠን አትመለስምን?
ሕዝብም በአንተ ደስ ይላቸዋል።
8አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህን አሳየን፥
አቤቱ፥ ማዳንህንም አሳየን።
9እግዚአብሔር የሚናገረውን እሰማለሁ፥
ወደ እብደታቸው ካልተመለሱ በቀር
ጌታ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ይናገራልና።
10ነገር ግን ክብር በምድራችን ያድር ዘንድ
ማዳኑ ለሚፈሩት ቅርብ ነው።
11 # መዝ. 89፥15፤ 97፥2። ጽኑ ፍቅርና እውነት ተገናኙ፥
ጽድቅና ሰላም ተቃቀፉ።
12 # ኢሳ. 45፥8። እውነት ከምድር በቀለች፥
ጽድቅም ከሰማይ ተመለከተች።
13 # መዝ. 67፥7፤ ዘሌ. 26፥4፤ ሕዝ. 34፥27፤ ሆሴዕ 2፥23-24፤ ዘካ. 8፥12። ጌታም በጎ ነገርን ይሰጣል፥
ምድራችንም ፍሬዋን ትሰጣለች።
14ጽድቅ በፊቱ ይሄዳል፥
የእርምጃውንም ዱካ በመንገድ ውስጥ ያኖራል።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ