የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 79

79
1የአሳፍ መዝሙር።
# 2ነገ. 25፥9-10፤ ሰቆ.ኤ. 1፥10። አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፥
ቅዱሱን መቅደስህንም አረከሱ፥
ኢየሩሳሌምንም አፈራረሱአት።
2 # ኤር. 7፥33። የባርያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥
የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፥
3 # 1መቃ. 7፥17፤ ኤር. 14፥16። ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥
የሚቀብራቸውም አጡ።
4 # መዝ. 44፥14፤ 80፥7፤ 123፥3-4፤ ኢዮብ 12፥4፤ ዳን. 9፥16፤ ሶፎ. 2፥8። ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥
በዙሪያችንም ላሉ መሳቂያና መሳለቂያ።
5 # መዝ. 13፥2፤ 44፥24፤ 89፥47፤ ዘዳ. 4፥24። አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘለዓለም ትቈጣለህ?
ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል?
6 # መዝ. 14፥4፤ ኤር. 10፥25። በማያውቁህ አሕዛብ ላይ፥
ስምህንም በማይጠሩ መንግሥታት ላይ መዓትህን አፍስስ፥
7ያዕቆብን በልተውታልና፥
መኖርያውንም ባድማ አድርገዋልና።
8 # መዝ. 142፥7። የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥
ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥
እጅግ ተዋርደናልና።
9 # ሕዝ. 20፥44፤ 36፥22። አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን፥
ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥
ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን።
10 # መዝ. 42፥4፤ 115፥2፤ ኢዩ. 2፥17። አሕዛብ፦ “አምላካቸው ወዴት ነው?” ለምን ይበሉ፥
የፈሰሰውን የባርያዎችህን ደም በቀል
በዐይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ።
11 # መዝ. 102፥21። የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፥
እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን።
12 # መዝ. 89፥51-52። አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን
ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።
13እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማርያህም በጎች፥
ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፥
ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ