መዝሙረ ዳዊት 79
79
1የአሳፍ መዝሙር።
#
2ነገ. 25፥9-10፤ ሰቆ.ኤ. 1፥10። አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፥
ቅዱሱን መቅደስህንም አረከሱ፥
ኢየሩሳሌምንም አፈራረሱአት።
2 #
ኤር. 7፥33። የባርያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥
የጻድቃንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት፥
3 #
1መቃ. 7፥17፤ ኤር. 14፥16። ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥
የሚቀብራቸውም አጡ።
4 #
መዝ. 44፥14፤ 80፥7፤ 123፥3-4፤ ኢዮብ 12፥4፤ ዳን. 9፥16፤ ሶፎ. 2፥8። ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥
በዙሪያችንም ላሉ መሳቂያና መሳለቂያ።
5 #
መዝ. 13፥2፤ 44፥24፤ 89፥47፤ ዘዳ. 4፥24። አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘለዓለም ትቈጣለህ?
ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል?
6 #
መዝ. 14፥4፤ ኤር. 10፥25። በማያውቁህ አሕዛብ ላይ፥
ስምህንም በማይጠሩ መንግሥታት ላይ መዓትህን አፍስስ፥
7ያዕቆብን በልተውታልና፥
መኖርያውንም ባድማ አድርገዋልና።
8 #
መዝ. 142፥7። የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥
ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥
እጅግ ተዋርደናልና።
9 #
ሕዝ. 20፥44፤ 36፥22። አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን፥
ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥
ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን።
10 #
መዝ. 42፥4፤ 115፥2፤ ኢዩ. 2፥17። አሕዛብ፦ “አምላካቸው ወዴት ነው?” ለምን ይበሉ፥
የፈሰሰውን የባርያዎችህን ደም በቀል
በዐይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ።
11 #
መዝ. 102፥21። የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፥
እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን።
12 #
መዝ. 89፥51-52። አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን
ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።
13እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማርያህም በጎች፥
ለዘለዓለም እናመሰግንሃለን፥
ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 79: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ