መዝሙረ ዳዊት 74
74
1የአሳፍ ትምህርት።
#
መዝ. 10፥1፤ 44፥24፤ 77፥8፤ መዝ. 80፥5። አቤቱ፥ ስለምን ለሁልጊዜ ጣልኸኝ?
በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቁጣህ ስለምን ጨሰ?
2 #
መዝ. 68፥17፤ 132፥13፤ ዘፀ. 15፥17፤ ኤር. 10፥16፤ 51፥19። አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥
የተቤዠሃትንም የርስትህን በትር፥
በእርሷ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ አስብ።
3መጠን ወደሌላቸው ፍርስራሶች እርምጃህን አቅና፥
ጠላት በመቅደስ ያለውን ሁሉ አጥፍቶአል።
4ጠላቶችህ በአደባባይህ#74፥4 ግሪኩ “በዓልህ” ይላል። ላይ አገሡ፥
ለድል ምልክት ዐላማቸውን አኖሩ።
5በላይኛው መግቢያ ውስጥ፥
በዱር፥ በመጥረቢያ እንጨቶችን የሚቆርጡ ሰዎችን ይመስላሉ።
6እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት።
7 #
መዝ. 79፥1፤ ኢሳ. 64፥10። መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ፥
የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ።
8አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው፦
ኑ፥ የእግዚአብሔርን የተቀድሱ ቦታዎችን አቃጠሉ።
9 #
ሰቆ.ኤ. 2፥9። ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ አይኖርም፥
ይህም እስከ መቼ እንደሚቆይ የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም።
10 #
መዝ. 89፥47። አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል?
ስምህን ጠላት ለሁልጊዜ ያቃልላልን?
11እጅህንም ለምን ትመልሳለህ?
ቀኝ እጅህንም ለምን በብብትህ መካከል ታቆያለህ?
12እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥
በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ።
13 #
ዘፀ. 14፥21፤ ኢሳ. 51፥9-10። አንተ ባሕርን በኃይልህ ከፈልካት፥
የአውሬዎችን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ።
14 #
ኢዮብ 41፥1፤ መዝ. 104፥26፤ ኢሳ. 27፥1። አንተ የዘንዶውን#74፥14 ሌዋታን ራሶች ቀጠቀጥህ፥
ለኢትዮጵያ ሰዎችም#74፥14 የዕብራይስጡ ዘር “ለምድረ በዳ ሰዎች” ይላል። እንደ ምግብ ሰጠሃቸው።
15አንተ ምንጮቹንና ፈሳሾቹን ሰነጠቅህ፥
አንተ ሁልጊዜ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅህ።
16 #
ዘፍ. 1። ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፥
አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ።
17አንተ የምድርን ዳርቻ ሁሉ አረጋገጥህ፥
በጋንም ክረምትንም አንተ ሠራህ።
18ይህንንም አስታውስ፥
ጠላት በጌታ ተሳለቀ፥
አላዋቂ ሕዝብም በስምህ ቀለደ።
19የምትገዛልህን እርግብ ለአራዊት አትስጣት፥
የችግረኞችህን ነፍስ መቼውንም አትርሳ።
20ወደ ኪዳንህ ተመልከት፥
የምድር የጨለማ ስፍራዎች በዓመፅ ቤቶች ተሞልተዋልና።
21ችግረኛ አፍሮ አይመለስ፥
ችግረኛና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ።
22አቤቱ፥ ተነሥ በቀልህንም ተበቀል፥
አላዋቂዎች ዘወትር የተሳለቁብህን አስብ።
23የጠላቶችህን ቃል አትርሳ፥
የተቃዋሚዎችህ ድንፋታ ሳያቋርጥ ወደ አንተ ይወጣል።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 74: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ