የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 7:1-9

መዝሙረ ዳዊት 7:1-9 መቅካእኤ

አቤቱ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥ ነፍሴን እንደ አንበሳ ነጥቀው እንዳይሰብሩዋት፥ የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር። አቤቱ አምላኬ፥ እንዲህ አድርጌ ከሆነ፥ ዓመፃም በእጄ ቢኖር፥ መልካም ላደረጉልኝም ክፉን መልሼላቸው ከሆነ፥ ጠላቴንም በከንቱ ገፍቼው ከሆነ፥ ጠላት ነፍሴን ያሳድዳት ያግኛትም፥ ሕይወቴንም በምድር ላይ ይርገጣት፥ ክብሬንም በትቢያ ላይ ያዋርዳት። አቤቱ፥ በመዓትህ ተነሥ፥ በጠላቶቼ ላይ በቁጣ ተነሣባቸው፥ አቤቱ አምላኬ፥ ባዘዝኸው ትእዛዝ ንቃ። የአሕዛብም ጉባኤ ይከብብሃል፥ በእነርሱም ላይ ወደ ከፍታ ተመለስ። ጌታ በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል፥ አቤቱ፥ እንደጽድቄ ፍረድልኝ፥ እንደ የዋህነቴም ይሁንልኝ።