መዝሙረ ዳዊት 66:17-20

መዝሙረ ዳዊት 66:17-20 መቅካእኤ

በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፥ በአንደበቴም አመሰገንሁት። በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን ጌታ አይሰማኝም ነበር። ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ፥ የልመናዬን ድምፅ አደመጠ። ጸሎቴን ያልከለከለኝ ቸርነቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን።