የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 66

66
1ለመዘምራን አለቃ፥ የመነሣት የምስጋና መዝሙር።
2 # መዝ. 65፥14፤ ኢሳ. 44፥23። በምድር ያላችሁ ሁሉ ለእግዚአብሔር እልል በሉ፥
ለስሙም ዘምሩ፥ ለምስጋናውም ክብርን ስጡ።
3 # መዝ. 18፥45፤ ሚክ. 7፥17። እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው፥
ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ።
4በምድር ያሉ ሁሉ ለአንተ ይሰግዳሉ፥
ለአንተም ይዘምራሉ፥
ለስምህም ይዘምራሉ።”
5ኑ የእግዚአብሔርንም ሥራ እዩ፥
ከሰው ልጆች ይልቅ በግብሩ#66፥5 በምክሩ ግሩም ነው።
6 # መዝ. 74፥15፤ 114፥3፤ ዘፀ. 14፥21፤ ኢያ. 3፥14፤ ኢሳ. 44፥27፤ 50፥2። ባሕርን የብስ አደረጋት፥
ወንዙንም በእግር ተሻገሩ፥
በዚያ በእርሱ ደስ ይለናል።
7በኃይሉ ለዘለዓለም ይገዛል፥
ዐይኖቹ ወደ አሕዛብ ይመለከታሉ፥
ዓመፀኞች ራሳቸውን ከፍ ከፍ አያድርጉ።
8አሕዛብ ሆይ፥ አምላካችንን ባርኩ፥
የምስጋናውንም ድምፅ አሰሙ።
9 # መዝ. 91፥12፤ 121፥3፤ 1ሳሙ. 2፥9፤ ምሳ. 3፥23። ነፍሴን በሕይወት ያኖራታል፥
እግሮቼንም ለመናወጥ አልሰጠም።
10 # ኢሳ. 48፥10። አቤቱ፥ ፈትነኸናልና፥
ብርንም እንደሚያነጥሩት አንጥረኸናልና።
11ወደ ወጥመድ አገባኸን፥
በጀርባችንም መከራን አኖርህ።
12 # ኢሳ. 43፥2። ሰው በራሳችን ላይ እንዲረማመድ አደረግህ፥
በእሳትና በውኃ መካከል አለፍን፥
ወደ በረከትም አወጣኸን።
13-14ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ወደ ቤትህ እገባለሁ፥
በመከራዬ ጊዜ በአፌ የተናገርሁትን
በከንፈሮቼም ቃል የገባሁልህን
ስእለቴን እፈጽማለሁ።
15ከወጠጤዎች መዓዛ ጋር
ለሚቃጠል መሥዋዕት ፍሪዳን አቀርባለሁ፥
ላሞችንና ፍየሎችን እሠዋልሃለሁ።
16እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ፥
ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።
17በአፌ ወደ እርሱ ጮኽሁ፥
በአንደበቴም አመሰገንሁት።
18በልቤስ በደልን አይቼ ብሆን
ጌታ አይሰማኝም ነበር።
19ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ፥
የልመናዬን ድምፅ አደመጠ።
20ጸሎቴን ያልከለከለኝ
ቸርነቱንም ከእኔ ያላራቀ
እግዚአብሔር ይመስገን።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ