የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 65

65
1ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት የምስጋና መዝሙር።
2አቤቱ፥ በጽዮን ለአንተ ምስጋና ይገባል፥
ለአንተም ስእለት ይቀርባል።
3 # ኢሳ. 66፥23። ጸሎትን ወደምትሰማ ወደ አንተ ሥጋ ሁሉ ይመጣል።
4 # መዝ. 32፥1-2፤ 78፥38፤ ኢሳ. 1፥18። የዓመፃ ነገር በረታብን፥
መተላለፋችንንስ አንተ ይቅር ትላለህ።
5አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፥
ከቤትህ፥ ከቅዱስ መቅደስህ፥ በረከት እንጠግባለን።
6 # ኢሳ. 66፥19። በምድር ዳርቻ ሁሉና በሩቅ ባሕር ውስጥ ላሉ ተስፋቸው የሆንህ
አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ በጽድቅ፥ በድንቅ ነገሮች መለስክልን።
7በጉልበትህ ተራሮችን አጸናሃቸው፥
በኃይልም ታጥቀሃል።
8 # መዝ. 89፥10፤ 107፥29፤ ኢዮብ 38፥11፤ ኢሳ. 17፥12፤ ማቴ. 8፥26። የባሕሩን ማጓራት፥ የሞገድንም ጩኸት፥
የአሕዛብንም ማጉረምረም ዝም ታሰኛለህ።
9ከተኣምራትህ የተነሣ በምድር ዳርቻ የሚኖሩ ይፈራሉ፥
የጥዋትንና የማታን መውጫዎች#65፥9 ምሥራቅንና ምዕራብን ደስ ታሰኛቸዋለህ።
10 # ዘሌ. 26፥4፤ ኢሳ. 30፥23፤ 25፤ ኢዩ. 2፥22-23። ምድርን ጐበኘሃት አጠጣሃትም፥
ብልጥግናዋንም እጅግ አበዛህ፥
የእግዚአብሔር ወንዝ ውኃን የተመላ ነው፥
ምግባቸውን አዘጋጀህ፥ እንዲሁ ታሰናዳለህና።
11ትልምዋን ታረካለህ፥
ቦይዋንም ታስተካክላለህ፥
በነጠብጣብ ታለሰልሳታለህ፥
ቡቃያዋንም ትባርካለህ።
12በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥
ፈለጎችህ ስብን ይጠግባሉ።
13የምድረ በዳ መስኮች ይረካሉ፥
ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ።
14 # ኢሳ. 44፥23። ማሰማርያዎች መንጎችን ለበሱ፥
ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፥
በደስታ ይጮኻሉ ይዘምራሉም።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}