መዝሙረ ዳዊት 60
60
1ለመዘምራን አለቃ፥ ለትምህርት የዳዊት ቅኔ። 2#2ሳሙ. 8፥2-3፤13፤ 1ዜ.መ. 18፥2፤3፤12።የሶርያን ሁለቱን ወንዞችና የሶርያን ሶባልን ባቃጠለ ጊዜ ኢዮአብም ተመልሶ ከኤዶማውያን ሰዎች በጨው ሸለቆ ዐሥራ ሁለት ሺህ በገደለ ጊዜ፥
3አቤቱ፥ ጣልኸን አፈረስኸንም፥
ተቈጣኸን ጠግነን።
4 #
መዝ. 75፥4፤ ኢሳ. 24፥19። ምድርን አናወጥሃት አወክሃትም፥
ተናውጣለችና ቁስልዋን ፈውስ።
5 #
መዝ. 75፥9፤ ኢሳ. 51፥17፤21-22፤ ኤር. 25፥15። ለሕዝብህ ጭንቅን አሳየሃቸው፥
አስደንጋጩንም ወይን አጠጣኸን።
6ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ፥
ለሚፈሩህ ምልክትን ሰጠሃቸው።
7ወዳጆችህ እንዲድኑ
በቀኝህ አድን፥ አድምጠኝም።
8እግዚአብሔር በቅድስናው#60፥8 “በመቅደሱ” የሚሉ እትሞች አሉ ተናገረ፥
“በድል መንፈስ፥ ሴኬምንም እከፋፍላለሁ፥
የሱኮትንም ሸለቆ እለካለሁ።
9ገለዓድ የእኔ ነው፥ ምናሴም የእኔ ነው፥
ኤፍሬም የራሴ ቁር ነው።
ይሁዳ ንጉሤ በትሬ ነው፥
10 #
ሩት 4፥7-8፤ መዝ. 108፥9። ሞዓብ መታጠቢያ ሳህኔ ነው፥
በኤዶምያስ ላይ ጫማዬን እዘረጋለሁ፥
በፍልስጥኤም ላይ በድል እጮኻለሁ።
11ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል?
ማንስ እስከ ኤዶምያስ ይመራኛል?”
12 #
መዝ. 44፥10። አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን?
አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
13በመከራችን ረድኤትን ስጠን
የሰውም ማዳን ከንቱ ነው።
14በእግዚአብሔር ኃይልን እናደርጋለን፥
እርሱ የሚያስጨንቁንን ያዋርዳቸዋልና።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 60: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ