የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 55

55
1ለመዘምራን አለቃ፥ በበገናዎች፥ የዳዊት ትምህርት።
2 # መዝ. 5፥2-3፤ 86፥6፤ 130፥1-2፤ ሰቆ.ኤ. 3፥56፤ ዮናስ 2፥3። አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥
ልመናዬንም ቸል አትበል።
3ተመልከተኝ መልስም ስጠኝ፥
በኀዘኔ ተቅበዘበዝሁ ተናወጥሁም፥
4ከጠላት ድምፅ ከዓመፀኛም ግፍ የተነሣ፥
ዓመፃን በላዬ ጥለውብኛልና፥ በቁጣም ጠልተውኛልና።
5ልቤ በላዬ ተናወጠብኝ፥
የሞት ድንጋጤም ወደቀብኝ።
6ፍርሃትና እንቅጥቅጥ መጡብኝ፥
መዘግነን#55፥6 ግሪኩ ጨለማ ይላል ሸፈነኝ።
7 # መዝ. 11፥1። በርሬ ዐርፍ ዘንድ እንደ ርግብ ክንፍን ማን በሰጠኝ!
8 # ኤር. 9፥1፤ ራእ. 12፥6። እነሆ፥ ኰብልዬ በራቅሁ በምድረ በዳም በተቀመጥሁ፥
9ከዐውሎና ከብርቱ ንፋስ ሸሽቼ በፈጠንሁ አልሁ።
10አቤቱ፥ ግፍንና ጠብን በከተማ ውስጥ አይቼአለሁና
አስጥማቸው አንደበታቸውንም ቁረጥ።
11በቀንና በሌሊት በቅጥርዋ ይከብቡአታል፥
በደልና ሁከት በመካከልዋ ነው፥
12 # ኤር. 5፥1፤ 6፥6፤ ሕዝ. 22፥2፤ ዕብ. 1፥3፤ ሶፎ. 3፥1። በውስጧ ጥፋት አለ፤
ተንኰልና ሽንገላ ከአደባባይዋ አይርቁም።
13ጠላትስ ቢሰድበኝ፥ በታገሥሁ ነበር፥
የሚጠላኝም ራሱን በላዬ ከፍ ከፍ ቢያደርግ፥
ከእርሱ በተሸሸግሁ ነበር።
14አንተ ግን፥ እኩያዬ ሰው፥
ባልንጀራዬና የልቤ ወዳጅ፥
15መብልን ከእኔ ጋር በአንድነት ያጣፈጥህ፥
በአንድ ልብ በእግዚአብሔር ቤት ተራመድን።
16 # መዝ. 49፥15፤ ዘኍ. 16፥33፤ ምሳ. 1፥2፤ ኢሳ. 5፥14። ሞት ይምጣባቸው፥
በሕይወት ሳሉ ወደ ሲኦል ይውረዱ፥
ክፋት በማደሪያቸውና በመካከላቸው ነውና።
17እኔ ግን ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥
ጌታም ያድነኛል።
18 # ዳን. 6፥11። በማታና በጥዋት በቀትርም አቤቱታ አቀርባለሁ
እጮኽማለሁ፥ ቃሌንም ይሰማኛል።
19በእኔ ላይ ብዙ ነበሩና
ከተቃጣብኝ ጦርነት ነፍሴን በሰላም ያድናታል።
20 # መዝ. 29፥10፤ 93፥2፤ ባሮክ 3፥3። አይለወጡምና፥ እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና
ከጥንት ጀምሮ የነበረ እግዚአብሔር ሰምቶ ያጐሰቁላቸዋል።
21ወዳጄ ከእርሱ ጋር ሰላም በነበሩት ላይ እጁን ዘረጋ፥
ኪዳኑንም#55፥21 የገባውንም ቃል አፈረሰ።
22 # መዝ. 12፥3፤ 28፥3፤ 57፥5፤ 62፥5፤ 64፥4፤ ምሳ. 26፥24-28፤ ኤር. 9፥7። አፉ ከቅቤ ይልቅ ለዘበ፥ በልቡ ውስጥ ግን ጦርነት ነበረ፥
ቃሎቹም ከዘይት ይልቅ ለሰለሱ፥
ነገር ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ናቸው።
23 # መዝ. 37፥5፤ ምሳ. 3፥5፤ 16፥3፤ 1ጴጥ. 5፥7። ሸክምህን በጌታ ላይ ጣል፥
እርሱም ይደግፍሃል፥
ለጻድቁም ለዘለዓለም ሁከትን አይሰጠውም።
24 # መዝ. 25፥2፤ 56፥4፤ 130፥5፤ መዝ. 28፥1፤ 30፥4፤ 40፥3፤ 88፥5፤ 143፥7፤ ምሳ. 1፥12፤ ዮናስ 2፥7። አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ታወርዳቸዋለህ፥
የደም ሰዎችና ሸንጋዮች ዘመናቸው ግማሽ አይሞላም፥
እኔ ግን፥ አቤቱ፥ በአንተ እታመናለሁ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ