የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 4

4
በእግዚአብሔር መታመን
1ለመዘምራን አለቃ በበገናዎች፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 118፥5። የጽድቄ አምላክ ሆይ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፥
በጭንቀቴም አሰፋህልኝ፥
ማረኝ፥ ጸሎቴንም ስማ።
3 # መዝ. 62፥4። እናንት የሰው ልጆች፥ እስከ መቼ ድረስ ክብሬን ታዋርዳላችሁ?#4፥3 የግሪኩ (የሰባ ሊቃናት) ትርጒም “ልባችሁን ታከብዳላችሁ” ይላል።
ከንቱ ነገርን ለምን ትወድዳላችሁ? ሐሰትንም ለምን ትሻላችሁ?
4በጻድቁ እንደ ተገለጠ እወቁ፥
ጌታ ወደ እርሱ በተጣራሁ ጊዜ ይሰማኛል።
5 # ኤፌ. 4፥26። ፍሩ#4፥5 የግሪኩ (የሰባ ሊቃናት) ትርጒም “ተቈጡ” ይላል።፥ ኃጢአትንም አትሥሩ፥
በመኝታችሁ ሳላችሁ በልባችሁ አስቡ፥ ዝምም በሉ።
6 # መዝ. 51፥19። የጽድቅን መሥዋዕት ሠዉ፥ በጌታም ታመኑ።
7 # መዝ. 31፥17፤ 44፥4፤ 67፥1፤ 80፥4፤ ኢዮብ 13፥24፤ ዘኍ. 6፥25፤ ዳን. 9፥17። በጎውን ማን ያሳየናል? የሚሉ ብዙ ናቸው።
አቤቱ፥ የፊትህን ብርሃን በላያችን አንሣ።
8በልቤ ደስታን ጨመርህ፥
ከስንዴ ፍሬያቸውና ከወይናቸው ይልቅ በዛ።
9 # መዝ. 3፥6። በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፥
አቤቱ፥ አንተ ብቻ በደኅንነት ታሳድረኛለህና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ