መዝሙረ ዳዊት 34
34
1ባሳደደው በአቤሜሌክ ፊት መልኩን በለወጠ ጊዜ በሄደም ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 #
መዝ. 145፥2። ጌታን ሁልጊዜ እባርከዋለሁ፥
ምስጋናውንም ዘወትር ከአፌ አይለይም።
3ነፍሴ በጌታ ትከብራለች፥
ገሮችም ሰምተው ደስ ይላቸዋል።
4ጌታን ከእኔ ጋር አክብሩት፥
በአንድነትም ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ።
5ጌታን ፈለግሁት መለሰልኝም፥
ከምፈራውም ሁሉ አዳነኝ።
6ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥
ፊታችሁም በፍጹም አያፍርም።
7ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ ጌታም ሰማው፥
ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
8 #
ዘፀ. 14፥19። የጌታ መልአክ ጌታን በሚፈሩት ሰዎች
ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።
9 #
መዝ. 2፥11፤ 1ጴጥ. 2፥3። ጌታ ቸር እንደሆነ ቅመሱ፥ እዩም፥
በእርሱ የሚታመን ሰው ብፁዕ ነው።
10 #
ምሳ. 3፥7። የሚፈሩት ምንም አያጡምና
ቅዱሳኑ ሁሉ፥ ጌታን ፍሩት።
11የአንበሳ ደቦሎች#34፥11 የግሪኩ ቅጂ “ባለ ጠጎች” ይላል። ተቸገሩ፥ ተራቡም፥
ጌታን የሚፈልጉት ግን መልካሙን ሁሉ አያጡም።
12 #
ምሳ. 1፥8፤ 4፥1። ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፥
ጌታን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
13 #
1ጴጥ. 3፥10-12። ሕይወትን የሚመኝ ሰው ማን ነው?
በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?
14አንደበትህን ከክፉ ነገር፥
ከንፈሮችህም ሽንገላን ከመናገር ከልክል።
15 #
መዝ. 37፥27። ከክፉ ነገር ሽሽ መልካምንም አድርግ፥
ሰላምን እሻ ተከተላትም።
16 #
መዝ. 33፥18። የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን
ጆሮዎቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።
17መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ
የጌታ ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ተነሥቶአል።
18ጻድቃን ጮኹ፥ ጌታም ሰማቸው
ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።
19ጌታ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፥
መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል።
20የጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፥
ጌታ ግን ከሁሉ ያድናቸዋል።
21 #
ዮሐ. 19፥36። አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል፥
ከእነርሱም አንድ አይሰበርም።
22ክፉዎቹን ክፋት ይገድላቸዋል
ጻድቃንንም የሚጠሉ ይፈረድባቸዋል።
23የባርያዎቹን ነፍስ ጌታ ይቤዣል፥
ወደ እርሱ የሚጠጉ ሁሉ አይፈረድባቸውም።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 34: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ