የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 31

31
1ለመዘምራን አለቃ፥ በማድነቅ ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር።
2 # መዝ. 71፥1-3። አቤቱ በአንተ ታመንሁ፥ ለዘለዓለም አልፈር፥
በጽድቅህም አድነኝ።
3ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ፈጥነህም አድነኝ፥
ታድነኝ ዘንድ መታመኛ አምላክና የመጠጊያ ቤት ሁነኝ።
4 # መዝ. 18፥2። አምባዬና መጠጊያዬ አንተ ነህና
ስለ ስምህ መንገዴን አቅና ምራኝም።
5አንተ መታመኛዬ ነህና
ከደበቁብኝ ወጥመድ አውጣኝ።
6 # ሉቃ. 23፥46፤ የሐዋ. 7፥59። በእጅህ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፥
የእውነት አምላክ አቤቱ፥ ተቤዥተኸኛል።
7ከንቱ ምናምንቴነትን የጠበቁትን ጠላህ፥
እኔ ግን በጌታ ታመንሁ።
8መከራዬን አይተሃልና፥
ነፍሴንም ከጭንቀት አድነሃታልና
በምሕረትህ ደስ ይለኛል ሐሤትም አደርጋለሁ።
9በጠላቴ እጅ አልዘጋኸኝም፥
በሰፊም ስፍራ እግሮቼን አቆምህ።
10 # መዝ. 10፥14። ተቸግሬአለሁና አቤቱ ምራኝ፥
ዓይኔም ከኀዘን የተነሣ ደከመ፥
ነፍሴም ሆዴም።
11 # መዝ. 32፥3፤ 38፥10-11። ሕይወቴ በኅዘን አልቃለችና፥
ዓመታቴም በልቅሶ ጩኸት፥
ኃይሌ በችግር ደከመ፥
አጥንቶቼም ተነዋወጡ።
12 # ኢዮብ 19፥13-19። በጠላቶቼ ዘንድ ተነወርኹ፥
ይልቁንም በጎረቤቶቼ ዘንድ፥
ለሚያውቁኝም ፍርሃት ሆንሁ፥
በሜዳ ያዩኝም ከእኔ ሸሹ።
13እንደ ሞተ ሰው ከልብ ተረሳሁ፥
እንደ ተበላሸ ዕቃም ሆንሁ።
14የብዙ ሰዎችን ስድብ ሰምቻለሁና፥
በዙሪያው ፍርሃት ነበረ፥
በላዬ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ
ነፍሴን ለመንጠቅ ተማከሩ።
15 # መዝ. 140፥7፤ ኢሳ. 25፥1። አቤቱ፥ እኔ ግን በአንተ ታመንሁ፥
አንተ አምላኬ ነህ አልሁ።
16ርስቴ በእጅህ ነው፥
ከጠላቶቼ እጅና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።
17 # መዝ. 67፥1፤ ዘኍ. 6፥24። ፊትህን በባርያህ ላይ አብራ፥
ስለ ምሕረትህም አድነኝ።
18አቤቱ፥ አንተን ጠርቻለሁና አልፈር፥
ክፉዎች ይፈሩ
በሲኦልም ዝም ይበሉ።
19 # መዝ. 12፥4። በድፍረትና በትዕቢት በመናቅም
በጻድቅ ላይ የሚናገሩ
የሽንገላ ከንፈሮች ድዳ ይሁኑ።
20በአንተ ለሚያምኑ በሰው ልጆች ፊት ያዘጋጀሃት
ለሚፈሩህም የሰወርሃት፥
ቸርነትህ እንደምን በዛች!
21 # መዝ. 27፥5። በፊትህ መጋረጃ ከሰው ክርክር ትጋርዳቸዋለህ፥
በድንኳንህም ከአንደበት ክርክር ትሸፍናቸዋለህ።
22በተከበበ ከተማ የሚያስደንቅ ምሕረቱን በእኔ የገለጠ
ጌታ ይመስገን።
23 # ዮናስ 2፥5። እኔስ ከዓይንህ ፊት ተጣልሁ፥
በድንጋጤ አልሁ፥
አንተ ግን ወደ አንተ በጮኽሁ ጊዜ
የልመናዬን ቃል ሰማኸኝ።
24ሁላችሁ ቅዱሳኑ፥ ጌታን ውደዱት፥
ጌታ እውነተኞችን ይፈልጋል፥
ትዕቢተኞችንም ፈጽሞ ይበቀላቸዋል።
25በጌታ የምታምኑ ሁላችሁ፥
በርቱ ልባችሁም ይጥና።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ