የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 25:8-15

መዝሙረ ዳዊት 25:8-15 መቅካእኤ

ጌታ ቸርና ቅን ነው፥ ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል። ትሑታንን በፍርድ ይመራል፥ ለትሑታን መንገድን ያስተምራቸዋል። የጌታ መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ። አቤቱ፥ በደሌ ብዙ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ። ጌታን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ እርሱን ያስተምረዋል። ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን ይወርሳል። ጌታ ለሚፈሩት ወዳጃቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል። እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና ዐይኖቼ ሁልጊዜ ወደ ጌታ ናቸው።