የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 150

150
1 # ዳን. 3፥53። ሃሌ ሉያ።
ጌታን በመቅደሱ አወድሱት፥
በኃይሉ ጠፈር#150፥1 በኀያሉ ሰማይ የሚገኘውን አምላክ አወድሱት።
2 # ዘዳ. 3፥24። ስለ ታላላቅ ሥራዎቹ አወድሱት፥
እንደ ታላቅነቱ ብዛት አወድሱት።
3 # መዝ. 81፥3-4፤ 149፥3፤ 2ሳሙ. 6፥5፤ 1ዜ.መ. 13፥8፤ 16፥5፤42፤ 2ዜ.መ. 5፥12-13፤ 7፥6። በመለከት ድምፅ አወድሱት፥
በበገናና በመሰንቆ አወድሱት።
4 # መዝ. 68፥26፤ ዘፀ. 15፥20። በከበሮና በሽብሸባ አወድሱት፥
በባለ አውታር መሣሪያና በእምቢልታ አወድሱት።
5ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አወድሱት፥
ድምፁ በሚሰማ ጸናጽል አወድሱት።
6 # ራእ. 5፥13። እስትንፋስ ያለው#150፥6 ሕይወት ያለው ሁሉ ጌታን ያወድስ።
ሃሌ ሉያ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ