መዝሙረ ዳዊት 129
129
1የዕርገት መዝሙር።
#
መዝ. 124፥1። እስራኤል፦ “ከትንሽነቴ ጀምሮ አብዝተው አጠቁኝ” ይበል፥
2 #
መዝ. 118፥13። ከትንሽነቴ ጀምሮ አብዝተው አጠቁኝ፥
ነገር ግን አላሸነፉኝም።
3 #
ኢሳ. 51፥23። አራሾች በጀርባዬ ላይ አረሱ፥
ትልማቸውን አስረዘሙ።#129፥3 ጅርባዬን በጅራፍ ተለተሉ
4ጌታ ጻድቅ ነው፥
የክፉዎችን ገመድ ቈረጠ።
5ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥
ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።
6 #
ኢሳ. 37፥27። በሰገነት ላይ እንደ በቀለ ሣር፥
ሳይነቀል እንደሚደርቅ፥
7ለሚያጭደው እጁን፥
ነዶዎቹን ለሚሰበስብ እቅፉን እንደማይሞላ ይሁኑ።
8 #
መዝ. 118፥26። በመንገድም የሚያልፉ፦ የጌታ በረከት በእናንተ ላይ ይሁን፥
በጌታ ስም እንመርቃችኋለን አይሉም።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 129: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ