መዝሙረ ዳዊት 122
122
1የዳዊት የዕርገት መዝሙር።
#
መዝ. 43፥3-4፤ 84፥2-5። ወደ ጌታ ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ።
2ኢየሩሳሌም ሆይ፥ እግሮቻችን በአደባባይሽ ቆሙ።
3 #
መዝ. 48፥13-14። ኢየሩሳሌምስ እርስ በርስዋ እንደ ተገጠገጠች ከተማ ተሠርታለች።
4 #
ዘዳ. 16፥16። የጌታን ስም ያመሰግኑ ዘንድ፥
ለእስራኤል ምስክር ሊሆኑ የጌታ ነገዶች ወደዚያ ይወጣሉ።
5ዙፋኖች በዚያ ለፍርድ ተቀምጠዋልና፥
የዳዊት ቤት ዙፋኖች።
6ለኢየሩሳሌም ሰላምን ለምኑ፥
አንተንም ለሚወድዱ መረጋጋት ይሁን።
7 #
መዝ. 128፥5። በቅጥሮችሽ ውስጥ ሰላም፥
በግምቦችሽም ውስጥ መረጋጋት ይሁን።
8 #
ዮሐ. 20፥19። ስለ ወንድሞቼ ስለ ባልንጀሮቼም፦
“በውስጥሽ ሰላም ይሁን” ልበል።
9ስለ ጌታ አምላካችን ቤት
ላንቺ መልካምነትሽን ፈለግሁ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 122: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ