የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መዝሙረ ዳዊት 118:1-7

መዝሙረ ዳዊት 118:1-7 መቅካእኤ

ሃሌ ሉያ! ጌታን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና። ቸር እንደሆነ፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም እንደሆነ የእስራኤል ቤት አሁን ይንገሩ። ቸር እንደሆነ፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም እንደሆነ የአሮን ቤት አሁን ይንገሩ። ቸር እንደሆነ፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም እንደሆነ ጌታን የሚፈሩ ሁሉ አሁን ይንገሩ። በተጨነቅሁ ጊዜ ጌታን ጠራሁት፥ መለሰልኝ፥ አሰፋልኝም። ጌታ ከጎኔ ነው፥ አልፈራም ሰው ምን ያደርገኛል? ጌታ ሊረዳኝ ከጎኔ ነው፥ እኔም ጠላቶቼን በኩራት አያለሁ።