መዝሙረ ዳዊት 116
116
1ሃሌ ሉያ! ጌታ የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት።
2ጆሮውን ወደ እኔ አዘንብሏልና
በዘመኔ ሁሉ እጠራዋለሁ።
3 #
መዝ. 18፥5፤ ዮናስ 2፥3። የሞት ገመዶች#116፥3 ሰባ ሊቃናት “የሞት ጣር ይላል”። ወጠሩኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፥
ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ።
4የጌታን ስም ጠራሁ፦
አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።
5 #
ዘፀ. 34፥6። ጌታ መሓሪና ጻድቅ ነው፥
አምላካችንም ርኅሩኅ ነው።
6ጌታ የዋሆችን ይጠብቃል፥
ተዋረድሁ፥ እርሱም አዳነኝ።
7 #
መዝ. 13፥6። ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፥
ጌታ መልካም አድርጎልሻልና፥
8 #
መዝ. 56፥14፤ ኢሳ. 25፥8፤ ራእ. 21፥4። በእርግጥም ነፍሴን ከሞት፥ ዓይኔንም ከእንባ፥
እግሬንም ከመሰናከል አድነሃል።
9 #
መዝ. 27፥13፤ 56፥14፤ ኢሳ. 38፥11። በሕያዋን አገር በጌታ ፊት እሄዳለሁ።
10 #
2ቆሮ. 4፥13። አመንሁ ስለዚህም ተናገርሁ፥
እኔም እጅግ ተቸገርሁ።
11 #
መዝ. 12፥2። እኔም ከድንጋጤዬ የተነሣ፦ “ሰው ሁሉ ሐሰተኛ ነው አልሁ”።
12ስላደረገልኝ መልካም ነገር ሁሉ ለጌታ ምንን እመልሳለሁ?
13የመድኃኒትን ጽዋ ከፍ አደርጋለሁ#116፥13 ሰባ ሊቃናት “እቀበላለሁ” ይላል።፥
የጌታንም ስም እጠራለሁ።
14በሕዝቡ ሁሉ ፊት፥ እነሆ ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ።
15 #
መዝ. 72፥14፤ ኢሳ. 43፥4። የቅዱሳኑ ሞት በጌታ ፊት የከበረ ነው።
16 #
መዝ. 86፥16፤ 143፥12፤ ጥበ. 9፥5። አቤቱ፥ እኔ አገልጋይህ ነኝ፥
አገልጋይህ፥ የሴት አገልጋይህም ልጅ ነኝ፤
ሰንሰለቴን ሰበርህ።
17 #
ዘሌ. 7፥12። ለአንተ የምስጋና መሥዋዕትን እሠዋለሁ፥
የጌታንም ስም እጠራለሁ።
18 #
ዮናስ 2፥10። በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ፥
19በጌታ ቤት አደባባይ፥ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በመካከልሽም እንዲሁ።
ሃሌ ሉያ።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 116: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ