መዝሙረ ዳዊት 1
1
1 #
መዝ. 26፥4-5፤ 40፥5። ብፁዕ ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥
በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥
በፌዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ።
2 #
ኢያ. 1፥8፤ መዝ. 119፤ ሲራ. 39፥1። ነገር ግን በጌታ ሕግ ደስ የሚለው፥
ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያስብ።
3 #
መዝ. 52፥10፤ 92፥13-15፤ ኤር. 17፥8። እርሱም በውኃ ፈሳሾች ዳር እንደ ተተከለ፥
ፍሬውን በየጊዜው እንደሚሰጥ፥
ቅጠሉም እንደማይረግፍ ዛፍ ይሆናል፥
የሚሠራውም ሁሉ ይከናወንለታል።
4 #
መዝ. 35፥5፤ 83፥14-16፤ ኢዮብ 21፥18። ክፉዎች እንዲህ አይደሉም፥
ነገር ግን ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው ትቢያ ናቸው።
5ስለዚህ ክፉዎች በፍርድ፥
ኃጢአተኞችም በጻድቃን ማኅበር አይቆሙም።
6 #
መዝ. 37፥18። ጌታ የጻድቃንን መንገድ ያውቃልና፥
የክፉዎች መንገድ ግን ትጠፋለች።
Currently Selected:
መዝሙረ ዳዊት 1: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ