መጽሐፈ ምሳሌ 7
7
1ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ
ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ።
2ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፥
ሕጌንም እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ፥
3በጣቶችህ እሰራቸው፥
በልብህ ጽላት ጻፋቸው።
4ጥበብን፦ “አንቺ እኅቴ ነሽ” በላት፥
ማስተማውልንም፦ “ዘመዴ” ብለህ ጥራት፥
5ከአምንዝራ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ፥
ቃሏን ካለዘበች ከሌላይቱ ሴት።
6በቤቴ መስኮት ሆኜ ወደ አደባባይ ተመለከትሁ፥
7ከአላዋቂዎች መካከል አስተዋልሁ፥
ከወጣቶችም መካከል አንዱ አእምሮ ጐድሎት አየሁ፥
8በአደባባይ ሲሄድ በቤትዋም አቅራቢያ ሲያልፍ፥
የቤትዋን መንገድ ይዞ ወደ እርሷ አቀና፥
9ማታ ሲመሽ፥ ጀምበር ስትጠልቅ፥
በሌሊትም በጽኑ ጨለማ።
10እነሆ፥ ሴት ተገናኘችው
የአምንዝራ ሴት ልብስ የለበሰች፥
ነፍሳትን ለማጥመድ የተዘጋጀች።
11ሁከተኛና እንቢተኛ ናት፥
እግሮችዋም በቤትዋ አይቀመጡም፥
12አንድ ጊዜ በጎዳና፥ አንድ ጊዜ በአደባባይ፥
በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች።
13ያዘችውም ሳመችውም፥
ፊትዋም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው፦
14“መሥዋዕትንና የደኅንነት ቁርባንን ማቅረብ ነበረብኝ፥
ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ።
15ስለዚህ እንድገናኝህ፥ ፊትህንም በትጋት ለመሻት ወጥቻለሁ፥
አግኝቼሃለሁም።
16በአልጋዬ ላይ ማለፊያ የአልጋ ልብስ ዘርግቼበታለሁ፥
የግብጽንም ያማሩ አልባሳት አንጥፌበታለሁ።
17በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ።
18ና፥ እስኪ ነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፥
በተወደደ መተቃቀፍም ደስ ይበለን።
19ባለቤቴ በቤቱ የለምና፥
ወደ ሩቅ መንገድ ሄዶአልና፥
20በእጁም የብር ከረጢት ወስዶአል፥
ሙሉ ጨረቃ በሆነች ጊዜ ወደ ቤቱ ይመለሳል።”
21በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፥
በከንፈርዋ ልዝብነት ትጐትተዋለች።
22እርሱ እንዲህ ስቶ ይከተላታል፥
በሬ ለመታረድ እንደሚነዳ፥
አጋዘን#7፥22 የግሪኩ ትርጒም “ውሻ” ይላል ቸኩሎ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ፥
23ወፍ ወደ ወጥመድ እንደሚጣደፍ፥
ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሆን ሳያውቅ፥
ፍላጻ ጉበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ።
24ልጆቼ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስሙኝ
የአፌንም ቃል አድምጡ።
25ልብህ ወደ መንገድዋ አያዘንብል
በጎዳናዋ አትሳት።
26ወግታ የጣለቻቸው ብዙ ናቸውና፥
እርሷም የገደለቻቸው እጅግ ብዙ ናቸው።
27ቤትዋ የሲኦል መንገድ ነው፥
ወደ ሞት ማደርያዎች የሚወርድ ነው።
Currently Selected:
መጽሐፈ ምሳሌ 7: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ