ልጄ ሆይ፥ ለጎረቤትህ ዋስ ብትሆን፥ ለእንግዳ ሰው ቃል ብትገባ፥ በአፍህ ቃል ከተጠመድህ፥ በአፍህ ቃል ከተያዝህ። ልጄ ሆይ፥ ይህን አድርግ ራስህንም አድን፥ በጎረቤትህ እጅ ወድቀሃልና፥ ፈጥነህ ሂድ፥ ጎረቤትህንም ነዝንዘው። ለዓይንህ እንቅልፍን ለሽፋሽፍቶችህም እንጉልቻን አትስጥ፥ እንደ ሚዳቋ ከአዳኝ እጅ፥ እንደ ወፍም ከአጥማጅ እጅ ትድን ዘንድ። አንተ ሰነፍ፥ ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን። አለቃና አዛዥ ገዢም ሳይኖራት መብሏን በበጋ ታሰናዳለች፥ መኖዋንም በመከር ትሰበስባለች። አንተ ሰነፍ፥ እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ? ጥቂት መተኛት፥ ጥቂት ማንቀላፋት፥ ለመተኛት ጥቂት እጅን ማጣጠፍ፥ እንግዲህ ድህነትህ እንደ ወንበዴ፥ ችጋርህም ሰይፍ እንደ ታጠቀ ሰው ይመጣብሃል።
መጽሐፈ ምሳሌ 6 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ ምሳሌ 6:1-11
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች