የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ምሳሌ 5:18-23

መጽሐፈ ምሳሌ 5:18-23 መቅካእኤ

ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፥ ከጉብዝናህም ሚስት ጋር ደስ ይበልህ። እንደ ተወደደች ዋላ እንደ ተዋበችም ሚዳቋ፥ ጡትዋ ሁልጊዜ ታርካህ፥ በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ። ልጄ ሆይ፥ ስለምን ጋለሞታ ሴት ትወድዳለህ? የሌላይቱንስ ብብት ለምን ታቅፋለህ? የሰው መንገድ በጌታ ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና። ክፉ በክፋቱ ይጠመዳል፥ በኃጢአቱም ገመድ ይታሰራል። አልተቀጣምና እርሱ ይሞታል፥ በአላዊቅነትም ብዛት ይስታል።