መጽሐፈ ምሳሌ 5:15-21

መጽሐፈ ምሳሌ 5:15-21 መቅካእኤ

ከጉድጓድህ ውኃ፥ ከምንጭህም የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ። ምንጮችህ ወደ ሜዳ፥ ወንዞችህ ወደ አደባባይ ይፈስሳሉን? ለአንተ ብቻ ይሁኑ፥ ከአንተ ጋር ላሉ እንግዶችም አይሁኑ። ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፥ ከጉብዝናህም ሚስት ጋር ደስ ይበልህ። እንደ ተወደደች ዋላ እንደ ተዋበችም ሚዳቋ፥ ጡትዋ ሁልጊዜ ታርካህ፥ በፍቅርዋም ሁልጊዜ ጥገብ። ልጄ ሆይ፥ ስለምን ጋለሞታ ሴት ትወድዳለህ? የሌላይቱንስ ብብት ለምን ታቅፋለህ? የሰው መንገድ በጌታ ፊት ነውና፥ አካሄዱንም ሁሉ እርሱ ይመለከታልና።