ኦሪት ዘኍልቊ 6
6
ናዝራውያን
1ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ወንድ ወይም ሴት ራሳቸውን ለጌታ ለመለየት የናዝራዊነት ስእለት ቢሳሉ፥ 3#ሉቃ. 1፥15።ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር መጠጥ ራሱን ይለይ፤ ከወይን ወይም ከሚያሰክር መጠጥ የሚሠራን ሆምጣጤ አይጠጣ፥ ማንኛውንም ዓይነት የወይን ዘለላ ጭማቂ አይጠጣ፤ የወይን ዘለላ ወይም ዘቢብ አይብላ። 4ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ከወይን ጠጅ የሚሠራውን ሌላ ነገር ሁሉ እንዲሁም የውስጡን ፍሬ ወይም ግልፋፊውን እንኳ አይብላ።
5“ራሱን ለመለየት ስእለት ባደረገበት ወራት ሁሉ በራሱ ላይ ምላጭ አይድረስበት፤ ለጌታ የተለየበት ወራት እስኪፈጸም ድረስ የተቀደሰ ይሆናል፥ የራሱንም ጠጉር ያሳድግ።
6“ለጌታ ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ወደ ሬሳ አይቅረብ። 7ለአምላኩ ያደረገው ቅድስና በራሱ ላይ ነውና አባቱ ወይም እናቱ ወይም ወንድሙ ወይም እኅቱ ሲሞቱ ራሱን ስለ እነርሱ አያርክስ። 8ራሱን በለየበት ወራት ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ነው።
9“ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት እርሱም የተቀደሰውን ራሱን ቢያረክስ፥ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጫል፤ በሰባተኛው ቀን ይላጨዋል። 10በስምንተኛውም ቀን ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ 11ካህኑም አንዱን ለኃጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርበዋል፤ በሬሳም የተነሣ ኃጢአት ሠርቶአልና ያስተሰርይለታል፥ በዚያም ቀን ራሱን ይቀድሰዋል። 12ራሱን የለየበትን ወራትም ለጌታ ይቀድሳል፥ የአንድ ዓመትም ተባት ጠቦት ለበደል መሥዋዕት ያመጣል፤ ናዝራዊነቱ ግን ረክሶአልና ያለፈው ወራት ሁሉ ከንቱ ይሆናል።
13 #
የሐዋ. 21፥23፤24። “የመለየቱ ወራት በተፈጸመ ጊዜ የናዝራዊው ሕግ ይህ ነው፤ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይቅረብ፤ 14ቁርባኑንም ለጌታ ያቅርብ፤ ነውር የሌለበት የአንድ ዓመት ተባት ጠቦት ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለባትን የአንድ ዓመት እንስት ጠቦት ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ነውርም የሌለበትን አውራ በግ ለአንድነት መሥዋዕት፥ 15አንድ ሌማትም እርሾ ያልገባበት እንጀራ፥ በዘይት የተለወሰ ከመልካም ዱቄትም የተሠሩ እንጐቻዎች፥ በዘይትም የተቀባ እርሾ ያልገባበት ስስ ቂጣ፥ የእህሉንም ቁርባን፥ የመጠጡንም ቁርባን ያቅርብ። 16ካህኑም በጌታ ፊት ያቀርባቸዋል፥ የኃጢአቱንም መሥዋዕት የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ያሳርግለታል። 17አውራውንም በግ ለአንድነት መሥዋዕት ከሌማቱ እርሾ ካልገባበት እንጀራ ጋር ወደ ጌታ ያቀርባል፤ ካህኑም ደግሞ የእህሉን ቁርባንና የመጠጡን ቁርባን ያቀርባል። 18ናዝራዊውም የተቀደሰውን የራሱን ጠጉር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ይላጫል፥ የተቀደሰውንም ራስ ጠጉር ወስዶ ከአንድነት መሥዋዕት በታች ወዳለው እሳት ይጥለዋል። 19ካህኑም የተቀቀለውን የአውራውን በግ ወርች፥ ከሌማቱም እርሾ ያልገባበትን አንድ የቂጣ እንጐቻ እርሾም ያልገባበትን አንድ ስስ ቂጣ ይወስዳል፥ የተቀደሰውንም የራስ ጠጉር ከተላጨ በኋላ በናዝራዊው እጆች ላይ ያኖራቸዋል፤ 20ካህኑም እነዚህን ለመወዝወዝ ቁርባን በጌታ ፊት ይወዘውዛቸዋል፤ ይህም ከሚወዘወዘው ፍርምባና ከሚቀርበው ወርች ጋር ለካህኑ የተቀደሰ ድርሻው ነው። ከዚያም በኋላ ናዝራዊው ወይን ሊጠጣ ይችላል።
21“ስእለቱን የተሳለው የናዝራዊ፥ የመግዛት አቅሙ ከሚፈቅድለት ሌላ ስለ ናዝራዊነቱ ለጌታ የሚያቀርበው የቁርባኑ ሕግ ይህ ነው፤ ስእለቱን እንደ ተሳለ እንደ ናዝራዊነቱ ሕግ እንዲሁ ያደርጋል።”
የካህናት ባርኮት
22ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 23“ለአሮንና ለልጆቹ እንዲህ ብለህ ተናገር፦ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦ 24ጌታ ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤ 25ጌታ ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤ 26ጌታ ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ። 27እነርሱም ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያኖራሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘኍልቊ 6: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ