መጽሐፈ ነህምያ 7
7
1እንዲህም ሆነ ቅጥሩ ከተሠራ በኋላ፥ በሮቹን ካቆምሁ በኋላ፥ በር ጠባቂዎች፥ መዘምራንና ሌዋውያን ተሾሙ፤ 2ወንድሜን ሐናኒንና የምሽጉ አዛዥ ሐናንያን በኢየሩሳሌም ላይ ኀላፊነት ሰጠኋቸው፤ እርሱም እውነተኛና ከሌሎች ይልቅ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ነበረ። 3እኔም እንዲህ አልኋቸው፦ የኢየሩሳሌም በሮች ፀሐይ ሞቅ እስኪል ድረስ አይከፈቱ፥ በሚቆሙበት ጊዜ በሮቹን ይዝጉ፥ ይቆልፉትም፤ ከኢየሩሳሌም ነዋሪዎች አንዳንዱን በተራው አንዳንዱን ደግሞ በየቤቱ አጠገብ ጠባቂዎች ይሾሙ። 4ከተማይቱ ሰፊና ታላቅ ነበረች፤ በውስጧ የነበሩ ሕዝብ ግን ጥቂቶች ነበሩ፤ ቤቶችም አልተሠሩም ነበር።
ከምርኮ የተመለሱ ሰዎች ስም ዝርዝር
5አምላኬም መኳንንቱን፥ ሹማምቱንና ሕዝቡን ሰብስቤ እንድቆጥራቸው በልቤ አስቀመጠ፤ አስቀድመው የመጡትን ሰዎች የትውልድ መጽሐፋቸውን አገኘሁ፥ በእርሱም እንደዚህ ተጽፎ አገኘሁ። 6#ዕዝ. 2፥1-70።የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከማረካቸው ምርኮኞች ወደ ኢየሩሳሌምና ወደ ይሁዳ ወደ ገዛ ከተማቸው የተመለሱት የአገር ልጆች እነዚህ ናቸው። 7ከዘሩባቤል፥ ከኢያሱ፥ ከነህምያ፥ ከዓዛርያ፥ ከራዓምያ፥ ከናሐማኒ፥ ከመርዶክዮስ፥ ከቢልሻን፥ ከሚስፌሬት፥ ከቢግዋይ፥ ከኔሑም፥ ከባዓና ጋር የመጡ የእስራኤል ሕዝብ የሰዎች ቍጥር ይህ ነው።
8የፓርዖሽ ልጆች፥ ሁለት ሺህ አንድ መቶ ሰባ ሁለት። 9የሽፋጥያ ልጆች ሦስት መቶ ሰባ ሁለት። 10የአራሕ ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ ሁለት። 11ከኢያሱና ከዮአብ ልጆች የሆኑ የፓሐት ሞዓብ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ዐሥራ ስምንት። 12የዔላም ልጆች፥ አንድ ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 13የዛቱ ልጆች፥ ስምንት መቶ አርባ አምስት። 14የዛካይ ልጆች፥ ሰባት መቶ ስድሳ። 15የቢኑይ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ስምንት። 16የቤባይ ልጆች፥ ስድስት መቶ ሀያ ስምንት። 17የዓዝጋድ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሀያ ሁለት። 18የአዶኒቃም ልጆች፥ ስድስት መቶ ስድሳ ሰባት። 19የቢግዋይ ልጆች፥ ሁለት ሺህ ስድሳ ሰባት። 20የዓዲን ልጆች፥ ስድስት መቶ አምሳ አምስት። 21የሕዝቅያስ ወገን የአጤር ልጆች፥ ዘጠና ስምንት። 22የሐሹም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ ስምንት። 23የቤጻይ ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ አራት። 24የሐሪፍ ልጆች፥ መቶ ዐሥራ ሁለት። 25የገባዖን#7፥25 ዕብራይስጡ ጊብዖን ይለዋል። ልጆች፥ ዘጠና አምስት። 26የቤተ ልሔምና የነጦፋ ሰዎች፥ መቶ ሰማንያ ስምንት። 27የዓናቶች ሰዎች፥ መቶ ሀያ ስምንት። 28የቤትዓዝማዌት ሰዎች፥ አርባ ሁለት። 29የቂርያትይዓሪም፥ የከፊራና የብኤሮት ሰዎች፥ ሰባት መቶ አርባ ሦስት። 30የራማና የጌባዕ ሰዎች፥ ስድስት መቶ ሀያ አንድ። 31የሚክማስ ሰዎች፥ መቶ ሀያ ሁለት። 32የቤቴኤልና የዓይ ሰዎች፥ መቶ ሃያ ሦስት። 33የሌላኛው ነቦ ሰዎች፥ አምሳ ሁለት። 34የሌላኛው ዔላም ልጆች ሺህ ሁለት መቶ አምሳ አራት። 35የሐሪም ልጆች፥ ሦስት መቶ ሀያ። 36የኢያሪኮ ልጆች፥ ሦስት መቶ አርባ አምስት። 37የሎድ፥ የሐዲድና የኦኖ ልጆች፥ ሰባት መቶ ሀያ አንድ። 38የሰናአ ልጆች፥ ሦስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሠላሳ።
39ካህናቱ፥ የኢያሱ ቤት የይዳዕያ ልጆች፥ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት። 40የኢሜር ልጆች፥ አንድ ሺህ አምሳ ሁለት። 41የፓሽሑር ልጆች፥ ሺህ ሁለት መቶ አርባ ሰባት። 42የሐሪም ልጆች፥ ሺህ ዐሥራ ሰባት።
43ሌዋውያኑ፥ የሆድዋ ወገን የኢያሱና የቃድሚኤል ልጆች፥ ሰባ አራት።
44መዘምራኑ፥ የአሳፍ ልጆች፥ አንድ መቶ አርባ ስምንት።
45በር ጠባቂዎች፥ የሻሉም ልጆች፥ የአጤር ልጆች፥ የጣልሞን ልጆች፥ የዓቁብ ልጆች፥ የሐጢጣ ልጆች፥ የሾባይ ልጆች፥ አንድ መቶ ሠላሳ ስምንት።
46የቤተ መቅደስ አገልጋዮች የጺሐ ልጆች፥ የሐሡፋ ልጆች፥ የጣባዖት ልጆች፥ 47የቄሮስ ልጆች፥ የሲዓ ልጆች፥ የፓዶን ልጆች፥ 48የልባና ልጆች፥ የሐጋባ ልጆች፥ የሻልማይ ልጆች፥ 49የሐናን ልጆች፥ የጊዴል ልጆች፥ የጋሐር ልጆች፥ 50የረአያ ልጆች፥ የረጺን ልጆች፥ የነቆዳ ልጆች፥ 51የጋዛም ልጆች፥ የዑዛ ልጆች፥ የፓሴሐ ልጆች፥ 52የቤሳይ ልጆች፥ የምዑኒም ልጆች፥ የነፉሽሲም ልጆች፥ 53የባቅቡቅ ልጆች፥ የሐቁፋ ልጆች፥ የሐርሑር ልጆች፥ 54የባጽሊት ልጆች፥ የምሒዳ ልጆች፥ የሐርሻ ልጆች፥ 55የባርቆስ ልጆች፥ የሲስራ ልጆች፥ የታማሕ ልጆች፥ 56የንጺሐ ልጆች፥ የሐጢፋ ልጆች።
57የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች፤ የሶጣይ ልጆች፥ የሶፌሬት ልጆች፥ የፕሪዳ ልጆች፥ 58የያዕላ ልጆች፥ የዳርቆን ልጆች፥ የጊዴል ልጆች፥ 59የሽፋጥያ ልጆች፥ የሐጢል ልጆች፥ የፖኬሬት ሃፅባይም ልጆች፥ የአሞን ልጆች። 60የቤተ መቅደስ አገልጋዮች ሁሉና የሰሎሞን አገልጋዮች ልጆች ሦስት መቶ ዘጠና ሁለት ነበሩ።
61ከቴልሜላሕ፥ ከቴል ሀርሻ፥ ከክሩብ፥ ከአዶንና ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤትና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፤ 62የድላያ ልጆች፥ የጦቢያ ልጆች፥ የንቆዳ ልጆች፥ ስድስት መቶ አርባ ሁለት። 63ከካህናቱም የሐባያ ልጆች፥ የሃቆጽ ልጆች፥ የባርዚላይ ልጆች እሱም ከገለዓዳዊው የባርዚላይ ሴቶች ልጆች ሚስት ያገባ፥ በስማቸውም የተጠራ ነው። 64እነዚህ በትውልድ መጽሐፍ ትውልዳቸውን ፈለጉ፥ ነገር ግን አልተገኘም፤ ከክህነትም ተከለከሉ። 65ገዢውም#7፥65 ቲርሻታ (የፋርስ የመዓረግ ሥም ነው)፦ በኡሪምና በቱሚም የሚፈርድ ካህን እስኪነሣ ደረስ ከተቀደሰው ነገር እንዳይበሉ ነገራቸው።
66ጉባኤው ሁሉ አንድ ላይ አርባ ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ስድሳ ነበር፥ 67ከወንድ አገልጋዮቻቸውና ከሴት አገልጋዮቻቸው ሌላ፥ ሰባት ሺህ ሦስት መቶ ሠላሳ ሰባት ነበሩ፥ ሁለት መቶ አርባ አምስት ወንዶችና ሴቶች መዘምራንም ነበሩአቸው። 68ግመሎቻቸው አራት መቶ ሠላሳ አምስት፥ አህዮቻቸው ስድስት ሺህ ሰባት መቶ ሀያ ነበሩ።#7፥68 ዕብራይስጡ በአንዳንድ ትርጉሞች እንዳለው ፈረሶችንና በቅሎዎችን አይጠቅስም። 69ከአባቶች አለቆች ለሥራው ስጦታ ሰጡ። አገረ ገዢውም አንድ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ አምሳ ድስቶች፥ አምስት መቶ ሠላሳ የካህናት ልብስ ለግምጃ ቤት ሰጠ።
70የአባቶች አለቆች ለሥራው ለግምጃ ቤት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክ፥ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ምናን ብር ሰጡ። 71የቀሩት ሕዝብ የሰጡት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብርና ስድሳ ሰባት የካህናት ልብስ ነበረ።
72ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ በር ጠባቂዎቹ፥ መዘምራኑ፥ ከሕዝቡ አንዳንዶቹ፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና እስራኤልም ሁሉ በገዛ ከተሞቻቸው ተቀመጡ፥ ሰባተኛውም ወር መጣ የእስራኤል ልጆችም በገዛ ከተሞቻቸው ተቀምጠው ነበር።
Currently Selected:
መጽሐፈ ነህምያ 7: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ