መጽሐፈ ነህምያ 6
6
የጠላቶች ሴራ መክሸፍ
1እንዲህም ሆነ ምንም እንኳ እስከዚያ ጊዜ ድረስ በበሮቹ ውስጥ ሳንቃዎቹን ባልገጥምም ቅጥሩን እንደሠራሁ፥ አንድም የፈረሰ እንዳልቀረ ሰንባላጥ፥ ጦቢያና ዓረባዊው ጌሼም የቀሩትም ጠላቶቻችን በሰሙ ጊዜ፥ 2ሰንባላጥና ጌሼም እንዲህ ብለው ላኩብኝ፦ “ናና በኦኖ ሜዳ ባሉት መንደሮች እንገናኝ፤” ነገር ግን ክፉ ሊያደርሱብኝ አቅደው ነበር። 3እኔም እንዲህ ብዬ መልእክተኞችን ላክሁባቸው፦ “ትልቅ ሥራ እሠራለሁ፥ መውረድም#6፥3 መምጣትም አልችልም። አልችልም፤ ሥራውን ትቼ ወደ እናንተ በመውረዴ ሥራው ለምን ይቆማል?” 4ይህንኑ ቃል#6፥4 መልዕክት። አራት ጊዜ ላኩብኝ፤ እኔም ይህንኑ ቃል መለስኩላቸው። 5ከዚህም በኋላ ሰንባላጥ የተከፈተ ደብዳቤ በእጁ አስይዞ ይህንኑ ቃል በአገልጋዩ ለአምስተኛ ጊዜ ላከብኝ፤ 6በውስጡ የተጻፈውም እንዲህ የሚል ነበር፦ “አንተና አይሁድ ልታምጹ እንዳቀዳችሁ፥ ለዚህም ቅጥሩን እንደሠራህ፥ ንጉሣቸውም ልትሆን እንደምትፈልግ በአሕዛብ ዘንድ ተሰምቶአል ጌሼምም ብሎታል። 7‘ንጉሥ በይሁዳ አለ’ ብለው ስለ አንተ በኢየሩሳሌም እንዲናገሩ ነቢያትን ሾመሃል፤ አሁንም ይህን ነገር በንጉሡ ዘንድ ይሰማል፤ ስለዚህ መጥተህ በአንድነት እንመካከር።” 8እኔም እንዲህ ብዬ ላክሁበት፦ “አንተ ከምትለው ነገር አንድም አልተደረገም፥ አንተ ከልብህ ፈጥረኸዋልና” 9ሁሉም እንዲህ እያሉ አስፈራሩን፦ “ከሥራው እጃቸውን ያላላሉ፥ አይሠራምም” አሁንም እጄን አበርታ#6፥9 አንዳንድ ትርጉሞች “አሁንም ጌታ ሆይ እጄን አብርታ” ይላሉ።።
10እኔም ወደ ሜሔጣብኤል ልጅ፥ ወደ ዴላያ ልጅ፥ ወደ ሼማዕያ ቤት ሄድሁ፤ እርሱም ተዘግቶ ነበርና፦ “በእግዚአብሔር ቤት፥ በመቅደሱ ውስጥ እንገናኝ፥ የመቅደሱንም በሮች እንዝጋ፤ ሊገድሉህ ይመጣሉና፥ በሌሊት ሊገድሉህ ይመጣሉና” አለ። 11እኔም፦ “እንደ እኔ ያለ ሰው ይሸሻልን? እንደ እኔ ያለ ነፍሱን ሊያድን ወደ መቅደስ የገባ ማን አለ? አልገባም” አልሁ። 12እነሆ እግዚአብሔር እንዳልላከው አወቅሁ፥ በእኔ ላይ ትንቢት የተናገረው ጦቢያና ሰንባላጥ ገዝተውት ስለ ነበረ ነው። 13ይህንም ነገር አደርግና እበድል ዘንድ፥ በእኔም ላይ ክፋት እንዲናገሩና እንዲያላግጡ ያስፈራራኝ። 14#ኤር. 23፥9-40፤ ዘካ. 13፥3።አምላኬ ሆይ፥ ጦቢያን፥ ሰንባላጥን ስለዚህ ሥራቸው ደግሞም ሊያስፈራሩኝ ነቢያቱን ኖዓድያና የተቀሩት ነቢያትን አስብ።
የቅጥሩ መጠናቀቅ
15ቅጥሩም በኤሉል ወር በሀያ አምስተኛው ቀን በአምሳ ሁለት ቀን ውስጥ ተጠናቀቀ። 16#መዝ. 118፥22-23፤ 127፥1።እንዲህም ሆነ፦ ጠላቶቻችን ሁሉ ይህን በሰሙ ጊዜ በዙሪያችን የነበሩ አሕዛብ ሁሉ ፈሩ፥ ዓይናቸውም እያየ ብዙ ውድቀት ሆነ፥ ይህ ሥራ በአምላካችን እንደ ተከናወነ አወቁ። 17ደግሞም በእነዚያ ቀኖች የይሁዳ መኳንንቶች ብዙ ደብዳቤዎቻቸውን ወደ ጦቢያ ይልኩ ነበር፥ የጦብያም ወደ እነርሱ ይመጡ ነበር። 18በይሁዳ ለእርሱ የማሉለት ብዙ ሰዎች ነበሩና፤ የአራሕ ልጅ የሼካንያ አማች ነበረና፥ ልጁ ይሆሐናንም የቤራክያን ልጅ የሜሹላምን ሴት ልጅ አግብቷልና። 19በተጨማሪም መልካም ሥራውን በፊቴ ይናገሩ ነበር፥ እኔ ያልሁትንም ለእርሱ ይነግሩት ነበር፤ ጦቢያም ሊያስፈራራኝ ደብዳቤዎችን ይልክ ነበር።
Currently Selected:
መጽሐፈ ነህምያ 6: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ