የYouVersion አርማ
የፍለጋ አዶ

መጽሐፈ ነህምያ 3

3
የሥራው ቅንጅት
1 # ኤር. 31፥38። ሊቀ ካህኑ ኤልያሺብና ወንድሞቹ ካህናት ተነሥተው “የበግ በር” ሠሩ፤ ቀደሱት፥ በሩንም አቆሙ፤ እስከ “ሜአ#3፥1 ሜአ ማለት መቶ ማለት ነው። ግንብ” እና እስከ “አሐናንኤል ግንብ” ድረስ ቀደሱት። 2በአጠገቡ የኢያሪኮ ሰዎች ሠሩ፤ በአጠገቡም የኢምሪ ልጅ ዛኩር ሠራ።
3 # ዕዝ. 2፥35፤ ሶፎ. 1፥10። የስናአ ልጆች “የዓሣ በር” ሠሩ፤ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ በሮቹን አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም ሠሩ። 4በአጠገባቸውም የቆጽ ልጅ የኡሪያ ልጅ ሜሬሞት አደሰ። በአጠገባቸውም የመሼዛቤል ልጅ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም አደሰ። በአጠገባቸውም የባዓና ልጅ ጻዶቅ አደሰ። 5በአጠገባቸውም ቴቁአውያን አደሱ፤ መኳንንቶቻቸው ግን ለጌታቸው ሥራ አንገታቸውን አልሰጡም#3፥5 በሥራው አልተሳተፉም።
6የፋሴሐ ልጅ ዮያዳ የቤሶዴያ ልጅ ሜሹላም “አሮጌ በር” አደሱ፤ ሰረገሎቹን አኖሩ፥ በሮቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አደረጉ። 7በአጠገባቸውም ጊብዖናዊው ሜላጥያ፥ ሜሮኖታዊው ያዶንና ከወንዙ ማዶ ያለው ገዢ ሥር የሆኑት የጊብዖንና የሚጽጳ ሰዎች አደሱ። 8በአጠገባቸውም ወርቅ አንጥረኛው የሐርሃያ ልጅ ዑዚኤል አደሰ። በአጠገቡም የሽቶ ቀማሚዎች ልጅ ሐናንያ አደሰ፤ እስከ ሰፊው ቅጥር ድረስ ኢየሩሳሌምን አደሱ። 9በአጠገባቸውም የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ ገዢ የሁር ልጅ ሬፋያ አደሰ። 10በአጠገባቸውም የሐሩማፍ ልጅ ዬዳያ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ። በአጠገቡም የሐሻቤኔያ ልጅ ሐጡሽ አደሰ። 11የሐሪም ልጅ ማልኪያና የፓሐት ሞዓብ ልጅ ሐሹብ ሌላውን ክፍልና “የእቶን ግንብ” አደሱ። 12በአጠገባቸውም እሱና ሴት ልጆቹ የኢየሩሳሌም ግዛት እኩሌታ ገዢ የሆነው የሃሎሔሽ ልጅ ሻሉም አደሰ።
13ሐኑንና የዛኖሐ ሰዎችም “የሸለቆ በር” አደሱ፤ መልሰው ሠሩት፥ ሳንቃዎቹንም አቆሙ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጁ፤ ደግሞም እስከ “የፍግ በር” ድረስ አንድ ሺህ ክንድ የሚሆን ቅጥር ሠሩ።
14የቤትሐካሪም አውራጃ ገዢ የሬካብ ልጅ ማልኪያ “የፍግ በር” አደሰ፤ መልሶ ሠራው፥ በሮቹን አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጀ።
15የሚጽጳም አውራጃ ገዢ የኮልሖዜ ልጅ ሻሉን “የምንጭ በር” አደሰ፤ መልሶ ሠራው፥ ከደነውም፥ በሮቹን አቆመ፥ ቁልፎቹንና መወርወሪያዎቹንም አበጀ፤ በንጉሡ አትክልት ቦታ አጠገብ ያለውን የሼላሕን መዋኛ ቅጥር ከዳዊት ከተማ ወደ ታች እስከሚወርደው ደረጃ ድረስ ሠራ። 16ከእርሱም በኋላ የቤትጹር አውራጃ እኩሌታ ገዢ የሆነው የዓዝቡቅ ልጅ ነህምያ በዳዊት መቃብር ፊት ለፊት እስካለው ስፍራ፥ እስከ ተሠራው መዋኛ ስፍራና እስከ ኃያላኑ ቤት ድረስ አደሰ። 17ከእርሱም በኋላ ሌዋውያንና የባኒ ልጅ ሬሑም አደሱ። በአጠገቡ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዢ ሐሻብያ ስለ አውራጃው ብሎ አደሰ። 18ከእርሱም በኋላ ወንድሞቻቸው፥ የቅዒላ አውራጃ እኩሌታ ገዚ የሆነው የሔናዳድ ልጅ ባዋይ አደሱ። 19በአጠገቡ የሚጽጳ ገዢ የኢያሱ ልጅ ዔዜር በግንቡ መደገፊያ ወደ ጦር መሣሪያ ግምጃ ቤት መወጣጫ ፊት ለፊት ያለውን ሁለተኛውን ክፍል አደሰ። 20ከእርሱም በኋላ የዛባይ ልጅ ባሮክ ሌላኛውን ክፍል ከግንቡ መደገፊያ ጀምሮ እስከ ታላቁ ካህን እስከ ኤልያሺብ ቤት መግቢያ ድረስ በቀናኢነት አደሰ። 21ከእርሱም በኋላ የቆጽ ልጅ የኡሪያ ልጅ ሜሬሞት ከኤልያሺብ ቤት በር ጀምሮ እስከ ኤልያሺብ ቤት መጨረሻ ድረስ ያለውን ክፍል አደሰ። 22ከእርሱ በኋላ የአካባቢው ሰዎች ካህናቱ አደሱ። 23ከእነርሱም በኋላ ብንያምና ሐሹብ ከቤታቸው ፊት ለፊት ያለውን አደሱ። ከእነርሱም በኋላ የአናንያ ልጅ የማዓሤያ ልጅ አዛርያ በቤቱ አጠገብ ያለውን አደሰ። 24ከእርሱም በኋላ የሔናዳድ ልጅ ቢኑይ ከዓዛርያ ቤት ጀምሮ እስከ የግንቡ መደገፊያ ድረስ ሌላውን ክፍል አደሰ። 25የኡዛይ ልጅ ፓላል በግንቡ መደገፊያ ፊት ለፊት ያለውንና በዘበኞች አደባባይ አጠገብ ከላይኛው የንጉሡ ቤት ወጥቶ የቆመውን ግንብ ሠራ፥ ከእርሱም በኋላ የፋኖስ ልጅ ፈዳያ ሠራ። 26በዖፌል የተቀመጡ የቤተ መቅደስ አገልጋዮች በምሥራቅ በኩል ካለው ከ “የውኃ በር” ፊት ለፊት ጀምሮ እስከ “የወጣው ግንብ” ድረስ አደሱ። 27ከእርሱም በኋላ ቴቁአውያን ታላቁ “የወጣው ግንብ” ፊት ለፊት ጀምሮ እስከ “ዖፌል ቅጥር” ድረስ ያለውን ሌላውን ክፍል አደሱ።
28ከ “የፈረሶች በር” በላይ ጀምሮ በየቤታቸው ትይዩ ያለውን ካህናቱ እያንዳንዳቸው አደሱ። 29#ሕዝ. 40፥6።ከዚያ በኋላ የኢሜር ልጅ ጻዶቅ ከቤቱ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ። ከእርሱም በኋላ “የምሥራቅ በር” ጠባቂ የሆነው የሼካኔያ ልጅ ሼማዔያ አደሰ። 30ከእርሱ በኋላ የሼሌምያ ልጅ ሐናንያና የጻላፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኑን ሌላውን ክፍል አደሱ። ከእርሱ በኋላ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም ከክፍሉ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ። 31ከእርሱም በኋላ የወርቅ አንጥረኛው ልጅ ማልኪያ ከ የቤተ መቅደስ አገልጋዮቹ ቤት፥ የነጋዴዎቹ ቤት ጀምሮ እስከ “የመሰብሰቢያ በር” ፊት ለፊት ያለውንና እስከ ማዕዘኑ ላይኛው ክፍል ድረስ አደሰ። 32ከማዕዘኑ ላይኛው ክፍል ጀምረው እስከ “የበግ በር” ድረስ ወርቅ አንጥረኞችና ነጋዴዎች አደሱ።
33ሳንባላጥ ቅጥሩን እየሠራን እንደሆነ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፥ ተበሳጨም፥ በአይሁድ ላይም አፌዘ። 34በወንድሞቹና በሰማርያ ሠራዊት ፊት፦ “እነዚህ ደካሞች አይሁድ ምን እየሠሩ ነው? ለራሳቸው መልሰው እየገነቡ ነው? መሥዋዕትን ሊያቀርቡ ነው? በአንድ ቀንስ ይጨርሱታል? የተቃጠለውንስ ድንጋይ ከፍርስራሹ መልሰው ሊያድኑት ነው?” አለ። 35አሞናዊው ጦብያ በአጠገቡ ቆሞ ነበር፥ እንዲህም አለ፦ “የሚገነቡት ቅጥራቸው ላይ ቀበሮ ቢወጣበት የድንጋይ ግንባቸውን ያፈርሰዋል፤” 36አምላካችን ሆይ፥ ተንቀናልና ስማ፤ ስድባቸውን በራሳቸው ላይ መልስባቸው፤ በምርኮ አገር እንዲበዘበዙ አሳልፈህ ስጣቸው። 37#ነህ. 6፥14፤ 13፥29፤ ኤር. 18፥23።በደላቸውን አትክደን፥ ኃጢአታቸውም ከፊትህ አይደምሰስ፤ ሠራተኞችን በፊታቸው አስቆጥተዋቸዋልና። 38ቅጥሩን ሠራን፤ የሕዝቡ ልብ ለሥራ ስለተነሣሣ ቅጥሩ ሁሉ እስከ እኩሌታው ድረስ ተጋጠመ።

ማድመቅ

Share

Copy

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ