መጽሐፈ ነህምያ 1:8-10

መጽሐፈ ነህምያ 1:8-10 መቅካእኤ

ለአገልጋይህ ለሙሴ እንዲህ ብለህ ያዘዝኸውን ቃል እባክህ አስብ። “ታማኞች ካልሆናችሁ በአሕዛብ መካከል እበትናችኋለሁ፤ ነገር ግን ወደ እኔ ብትመለሱ ትእዛዛቴን ብትጠብቁ ብትፈጽሟቸውም፥ ከእናንተ ውስጥ የሆኑ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ እንኳ ቢበተኑ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፥ ስሜ እንዲኖርበት ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።” እነዚህም በታላቁ ኃይልህና በብርቱ እጅህ የተቤዠሃቸው ባርያዎችህና ሕዝብህ ናቸው።