ትንቢተ ሚልክያስ መግቢያ

መግቢያ
ትንቢተ ሚልክያስ የተጻፈው ከክርስቶስ ልደት በፊት በአምስተኛው ምእተ ዓመት የኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ዳግመኛ ከተሠራ በኋላ ነበር። ነቢዩ አጥብቆ የሚያሳስበው ካህናቱም ሆኑ ሕዝቡ ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን ማደስ እንዳለባቸው ነበር፤ መጽሐፉ የእግዚአብሔር ሕዝብ በአኗኗሩም ሆነ በአምልኮቱ መረን የተለቀቀና የተበላሸ እንደ ነበር ይገልጻል። ካህናቱና ሕዝቡ ተገቢውን መሥዋዕት ባለማቅረብና በሰጣቸውም መመሪያ ባለመኖር እግዚአብሔርን ለማታለል ይሞክሩ ነበር። እግዚአብሔር መንገዱን ለማዘጋጀትና ቃል ኪዳኑን ለማወጅ መልእክተኛውን አስቀድሞ እንደሚልክና በሕዝቡ ላይ ለመፍረድ እንደሚመጣ ትንቢቱ ይናገራል። “እነሆ ነቢዩን ኤልያስን እልክላችኋለሁ” የሚለው ትንቢት በአይሁድና በክርስቲያኖች ዘንድ ትልቅ ተቀባይነት አግኝቷል። ይሄው ትንቢት በወንጌል ውስጥም ተጠቅሶ ይገኛል።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
1. ጌታ ለእስራኤል ሕዝብ ያለው ፍቅር (1፥1-5)
2. የእግዚአብሔር ፍርድ በካህናት ላይ (1፥6—2፥9)
3. የቃል ኪዳን መፍረስ (2፥10-17)
4. የጌታ መምጣት (3፥1-4)
5. እግዚአብሔርን ማታለል የማይገባ መሆኑ (3፥5-15)
6. የታማኞች መሸለምና የክፉዎች መቀጣት (3፥16—4፥6)
ምዕራፍ

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ