የሉቃስ ወንጌል 24:9-11

የሉቃስ ወንጌል 24:9-11 መቅካእኤ

ከመቃብሩም ተመልሰው ይህን ሁሉ ለዐሥራ አንዱና ለሌሎች ሁሉ ነገሩአቸው። ይህንንም ለሐዋርያት የነገሩአቸው መግደላዊት ማርያምና ዮሐና፥ የያዕቆብም እናት ማርያም፥ እንዲሁም ከእነርሱ ጋር የነበሩ ሌሎች ሴቶች ነበሩበት። ነገር ግን ይህ ቃል ቅዠት መስሎ ታያቸውና አላመኑአቸውም።