ኦሪት ዘሌዋውያን 22
22
የተቀደሰው ቁርባን ጥቅም
1ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 2“የተቀደሰውንም ስሜን እንዳያረክሱ፥ የእስራኤል ልጆች ለእኔ ከሚቀድሱአቸው ከቅዱሳን ነገሮች ራሳቸውን እንዲለዩ ለአሮንና ለልጆቹ ተናገር፤ እኔ ጌታ ነኝ። 3#ዘሌ. 7፥20-21።እንዲህ በላቸው፦ ‘በትውልዳችሁ ማናቸውም ሰው ከዘራችሁ ሁሉ ርኩሰት እያለበት የእስራኤል ልጆች ለጌታ ወደሚቀድሱት ወደ ቅዱሳን ነገሮች ቢቀርብ፥ ያ ሰው ከፊቴ ተለይቶ ይጥፋ፤ እኔ ጌታ ነኝ። 4#ዘሌ. 13—14፤ ዘሌ. 15፥2-18፤ ዘኍ. 19፥14-22፤ ዘሌ. 15፥16።ከአሮን ዘር ማናቸውም ሰው የለምጽ ደዌ ወይም ፈሳሽ ነገር ያለበት፥ ንጹሕ እስኪሆን ድረስ ከተቀደሱት ነገሮች አይብላ። በበድን፥ ወይም ዘሩ በሚፈስስበት ሰው የረከሰውን ነገር የሚነካ፥ 5#ዘሌ. 11፥29-31፤ ዘሌ. 15፥2-12፤18-27።ወይም የሚያረክሰውን ማናቸውንም የሚርመሰመስ ፍጥረት፥ ወይም ርኩሰቱ ማናቸውም ዓይነት ሆኖ የሚያረክሰውን ሰው የሚነካ፥ 6#ዘሌ. 17፥15፤ ዘኍ. 19፥7-8፤ 19፤ ዕብ. 10፥22።እንዲህ ያሉትን ሁሉ የሚነካ ሰው እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ገላውን በውኃ ካልታጠበ ከተቀደሰው አይብላ። 7#ዘዳ. 23፥12።ፀሐይም በገባች ጊዜ ንጹሕ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ እንጀራው ነውና ከተቀደሰው ነገር ይበላል። 8#ዘሌ. 11፥39-40፤ ሕዝ. 44፥31።በእርሱም እንዳይረክስ፥ የሞተውን አውሬም የገደለውን አይብላ፤ እኔ ጌታ ነኝ።’ 9#ዘሌ. 15፥31።ባረክሱት ጊዜ እንዳይሞቱ ስለ እርሱም ኃጢአትን እንዳይሸከሙ፥ ትዛዝን ይጠብቁ፤ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝ።
10 #
ማቴ. 12፥4። “ማናቸውም ምእመን ከተቀደሰው አይብላ የካህኑም እንግዳ የሆነ እና ተቀጥሮ የሚያገለግል ከተቀደሰው አይብላ። 11ካህኑ ግን ባርያ በገንዘቡ ቢገዛ እርሱ ይብላ፤ በቤቱም የተወለዱት ለእርሱ ከሆነው እንጀራ ይብሉ። 12የካህንም ልጅ ምእመንን ብታገባ፥ እርሷ ከተቀደሰው ቁርባን አትብላ። 13የካህን ልጅ ግን ባልዋ ቢሞት፥ ወይም ብትፋታ፥ ልጅም ባይኖራት፥ በብላቴንነትዋ እንደ ነበረች ወደ አባትዋ ቤት ብትመለስ፥ ከአባትዋ እንጀራ ትብላ፤ ማናቸውም ምእመን ግን ከእርሱ አይብላ። 14#ዘሌ. 5፥15-16።ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ከተቀደሰው ነገር ቢበላ በፊት በነበረው ላይ አምስት እጅ ጨምሮ የተቀደሰውን ነገር ለካህኑ ይስጥ። 15#ዘሌ. 19፥8፤ ዘኍ. 18፥32።ካህናቱ የእስራኤል ልጆች ለጌታ የሚያቀርቡትን የተቀደሰውን ነገር አያርክሱ፤ 16ከዚህም የተነሣ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝና የእነርሱን የተቀደሰ ነገር በሚበሉበት ጊዜ ኃጢአትንና በደልን እንዳይሸከሙ ነው።”
ተቀባይነት ያለው ቁርባን
17ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 18#ዘሌ. 1፥3።“ለአሮንና ለልጆቹ ለእስራኤልም ልጆች ሁሉ እንዲህ ብለህ ለእነርሱ ተናገር፦ ከእስራኤል ቤት ወይም ከእናንተ መካከል ከሚቀመጥ እንግዳ ማናቸውም ሰው ስእለቱን ሁሉ፥ ለጌታም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ በፈቃዱ የሚያቀርበውን ቁርባን ሁሉ ቢያቀርብ፥ 19#ዘሌ. 21፥16-23።እንዲሠምርላችሁ ከበሬ ወይም ከበግ ወይም ከፍየል መንጋ ነውር የሌለበትን ተባቱን አቅርቡ። 20#ዘዳ. 15፥21፤ 17፥1፤ ሚል. 1፥7-14።ነገር ግን አይሠምርላችሁምና ማናቸውም ነውር ያለበትን አታቅርቡ። 21#ዘሌ. 3፥1፤ 7፥11።ማናቸውም ሰው ከበሬ ወይም ከበግ መንጋ ስእለቱን ለመፈጸም ወይም በፈቃዱ ለማቅረብ የአንድነትን መሥዋዕት ለጌታ ቢያቀርብ፥ እንዲሠምርለት ፍጹም የሆነ ይሁን፥ በእርሱም ነውር የሆነ ነገር አይኑርበት። 22ዓይነ ስውር ወይም የተሰበረ ወይም አካለ ጎዶሎ ወይም የሚመግል ቁስል ወይም የእከክ ደዌ ያለበት ወይም ቋቁቻ የወጣበት ቢሆን፥ እነዚህን ሁሉ ለጌታ አታቅርቡ፤ እነርሱንም በእሳት የሚቀርብ ቁርባን አድርጋችሁ በመሠዊያው ላይ ለጌታ አትሠዉ። 23የበሬው ወይም የበጉ የአካሉ ክፍል ረጅም ወይም አጭር ቢሆን፥ ለፈቃድ መሥዋዕት ማቅረብ ትችላለህ፤ ለስእለት ግን አይሠምርም። 24የብልቱ ፍሬ የተሰነጋውን ወይም የተቀጠቀጠውን ወይም የተሰበረውን ወይም የተቈረጠውን ለጌታ አታቅርቡ፤ በምድራችሁም እነዚህን አትሠዉ። 25ከእንግዳም ሰው እጅ የተገኙ እንደነዚህ ያሉ እንስሶችን ሁሉ ለአምላካችሁ እንጀራ እንዲሆኑ አታቅርቡ፤ ርኩሰትም ነውርም አለባቸውና አይሠምሩላችሁም።”
26ጌታም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ 27#ዘፀ. 22፥29፤ 23፥19።“በሬ ወይም በግ ወይም ፍየል ሲወለድ ሰባት ቀን ከእናቱ ጋር ይቀመጥ፤ በስምንተኛውም ቀን ከዚያም በላይ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን ሆኖ ቢቀርብ የሠመረ ይሆናል። 28ላም ወይም በግ ብትሆን እርሷንና ልጇን በአንድ ቀን አትረዱ። 29የምስጋናንም መሥዋዕት ለጌታ ስትሠዉ እንዲሠምርላችሁ አድርጋችሁ ሠዉት። 30#ዘሌ. 7፥15።በዚያው ቀን ይበላል፤ ከእርሱ እስከ ነገ ምንም አትተዉ፤ እኔ ጌታ ነኝ። 31ስለዚህ ትእዛዛቴን ጠብቁ፥ አድርጉአቸውም፤ እኔ ጌታ ነኝ። 32እኔም በእስራኤል ልጆች መካከል እንድቀደስ የተቀደሰውን ስሜን አታርክሱ፤ የምቀድሳችሁ እኔ ጌታ ነኝ። 33እኔም አምላክ እንድሆናችሁ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ ጌታ ነኝ።”
Currently Selected:
ኦሪት ዘሌዋውያን 22: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ