ኦሪት ዘሌዋውያን 11

11
የሚበሉና የማይበሉ ምግቦች
1 # ዘሌ. 27፥11፤ 27፤ ዘፍ. 7፥2-3፤ 8—9፤ ዘዳ. 14፥3-21። ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ 2“ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብላችሁ ተናገሩ፦ በሕይወት ከሚኖሩ ከምድር እንስሶች ሁሉ የምትበሉአቸው እነዚህ ናቸው። 3ለሁለት የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውንና የሚያመሰኳውን እንስሳ ሁሉ ብሉ። 4#መሳ. 13፥4፤ 7፤ ኢሳ. 66፥17፤ ሕዝ. 4፥12-14።ነገር ግን ከሚያመሰኩት፥ ሰኮናቸውም ስንጥቅ ከሆነው ከእነዚህ አትበሉም፤ ግመል ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። 5ሽኮኮ ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። 6ጥንቸልም ያመሰኳል፥ ነገር ግን ሰኮናው ስላልተሰነጠቀ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። 7#ምሳ. 11፥22፤ ኢሳ. 65፥4፤ 66፥17፤ ማቴ. 7፥6፤ 8፥30-32፤ ማር. 5፥11-16፤ ሉቃ. 8፥32-33፤ 15፥15-16።እርያም ሰኮናው ለሁለት ተሰንጥቋል፥ ነገር ግን ስለማያመሰኳ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው። 8የእነዚህን ሥጋ አትበሉም፥ በድናቸውንም አትነኩም፤ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።
9 # ዮሐ. 21፥9-13። “በውኃ ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ እነዚህን ትበላላችሁ፤ በውኆች በባሕሮችም በወንዞችም ውስጥ ከሚኖሩት ሁሉ ክንፍና ቅርፊት ያላቸውን ትበላላችሁ። 10ነገር ግን በውኆች ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ፥ በውኆች ውስጥም በሕይወት ከሚኖሩ ነፍሳት፥ በባሕሮችና በወንዞች ውስጥ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸውን ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው። 11በእናንተም ዘንድ የተጸየፉ ይሆናሉ፤ ሥጋቸውንም አትብሉ፥ በድናቸውንም ተጸየፉ። 12በውኃ ውስጥ የሚኖሩ ክንፍና ቅርፊት የሌላቸው ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።
13“ከወፎችም ወገን የምትጸየፉአቸው እነዚህ ናቸው፤ አይበሉም፤ የተጸየፉ ናቸው፤ ንስር፥ ገዲ፥ ዓሣ አውጭ፥ 14ጭላት፥ ጭልፊት በየወገኑ፥ 15ቁራ ሁሉ በየወገኑ፥ 16ሰጎን፥ ጠላቋ፥ ዝዪ፥ በቋል በየወገኑ፥ 17ጉጉት፥ እርኩም፥ ጋጋኖ፥ 18የውኃ ዶሮ፥ ይብራ፥ ጥምብ አንሣ አሞራ፥ 19ሽመላ፥ ሳቢሳ በየወገኑ፥ ጅንጁላቴ ወፍ፥ የሌሊት ወፍ።
20“በአራት እግሮች የሚንቀሳቀሱ፥ ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው። 21ነገር ግን ከእግሮቻቸው በላይ በምድር ላይ የሚዘሉባቸው ጭኖች ካሉአቸው፥ በአራት እግሮች ከሚሄዱ ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት እነዚህን ትበላላችሁ። 22#ማቴ. 3፥4፤ ማር. 1፥6።ከእነርሱም እነዚህን ትበላላችሁ፤ አንበጣዎችን በየወገናቸው፥ ደጎብያዎችን በየወገናቸው፥ ፌንጣዎችን በየወገናቸው፥ ኲብኲባዎችን በየወገናቸው። 23ነገር ግን ሌሎች አራት እግሮች ያሉአቸው ጥቃቅን በራሪ ነፍሳት ሁሉ በእናንተ ዘንድ የተጸየፉ ናቸው።
በእስራኤል ዘንድ ርኩስ የሆኑ እንስሶች
24 # ዘሌ. 5፥2፤ 7፥21። “በእነዚህም የረከሳችሁ ትሆናላችሁ፤ የእነርሱንም በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 25በድናቸውንም የሚያነሣ ሁሉ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። 26ሰኮናውም የተከፈለ ሆኖ ነገር ግን ለሁለት ያልተሰነጠቀ፥ የሚያመሰኳም እንሰሳ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ እርሱንም የሚነካ ሁሉ ርኩስ ይሆናል። 27በአራት እግሮቹ ከሚሄድ እንስሳ ሁሉ መካከል፥ በመዳፎቹ ላይ የሚሄድ ሁሉ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው፤ የእርሱን በድን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 28በድናቸውንም የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል። እነርሱም በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው።
29“በምድር ላይም ከሚርመሰመሱ ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች መካከል እነዚህ በእናንተ ዘንድ ርኩሶች ናቸው፤ ሙጭልጭላ፥ አይጥ፥ እንሽላሊት በየወገኑ፥ 30ኤሊ፥ አዞ፥ ገበሎ፥ አርጃኖ፥ እስስት። 31ከሚንቀሳቀሱት ሁሉ መካከል በእናንተ ዘንድ ርኩሶች የሆኑት እነዚህ ናቸው። ከእነርሱም የሞተውን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 32ከእነርሱም የሞተው በማናቸውም ነገር ላይ ቢወድቅ እርሱ ርኩስ ይሆናል፤ የእንጨት ዕቃ ወይም ልብስ ወይም ቆዳ ወይም ከረጢት ቢሆን ለማናቸውም ሥራ የሚጠቅም ዕቃ ሁሉ በውኃ ውስጥ ይደረግ፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ግን ይነጻል። 33ከእነርሱም አንዱ በማናቸውም የሸክላ ዕቃ ውስጥ ቢወድቅ፥ በውስጡ ያለው ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እናንተም ዕቃውን ትሰብሩታላችሁ። 34እንዲህ ካለው ዕቃ ውኃ ፈስሶ የሚበላን ምግብ ሁሉ ከነካ ምግቡ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲህም ካለው ዕቃ ሁሉ ማናቸውም የሚጠጣ መጠጥ በውስጡ ካለ እርሱ ርኩስ ይሆናል። 35ከበድናቸውም የሚወድቅበት ነገር ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እቶን ወይም ምድጃ ቢሆን ይሰበር፤ ርኩሶች ናቸው፤ በእናንተም ዘንድ ርኩሶች ይሆናሉ። 36ነገር ግን ምንጭና የውኃ ማጠራቀምያ ጉድጓድ ንጹሕ ይሆናሉ፤ በድናቸውን ግን የሚነካ ርኩስ ይሆናል። 37ከበድናቸውም በሚዘራ በማናቸውም ዓይነት ዘር ላይ ቢወድቅ ዘሩ ንጹሕ ነው። 38ነገር ግን በዘሩ ላይ ውኃ ቢፈስበትና ከላዩም በድናቸው ቢወድቅበት፥ በእናንተ ዘንድ ርኩስ ነው።
39 # ዘሌ. 17፥15-16፤ 22፥8፤ ዘፀ. 22፥30፤ ሕዝ. 4፥12-14፤ 44፥31። “ለምግብነት ከምታውሉት እንስሳ የሞተ ቢኖር፥ በድኑን የሚነካ ሁሉ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል። 40#ዘሌ. 17፥15፤ 22፥8።ከበድኑም የሚበላ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል፤ እንዲሁም በድኑን የሚያነሣ ልብሱን ያጥባል፥ እስከ ማታም ድረስ ርኩስ ይሆናል።
41“በምድርም ላይ የሚርመሰመስ ተንቀሳቃሽ ሁሉ ጸያፍ ነው፥ አይበላም። 42በሆዱ የሚሳብ፥ በአራትም እግሮች የሚሄድ ወይም ብዙ እግሮች ያሉት፥ በምድርም ላይ የሚርመሰመሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ ጸያፍ ናቸውና አትብሉአቸው። 43#ዘሌ. 20፥25-26።በሚርመሰመሱ ተንቀሳቃሾች ሁሉ የገዛ አካላችሁን አታጸይፉ፤ እንዳትረክሱም የገዛ አካላችሁን በእነርሱ አታርክሱ። 44#ዘሌ. 19፥2፤ 20፥7፤ 26፤ ማቴ. 5፥48፤ 1ጴጥ. 1፥16።እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና፤ ስለዚህ ራሳችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤ በምድርም ላይ በደረታቸው እየተሳቡ በሚርመሰመሱ ሁሉ የገዛ አካላችሁን አታርክሱ። 45እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ ጌታ ነኝ፤ ስለዚህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።”
46የእንስሳና የወፍ፥ በውኃም ውስጥ የሚንቀሳቀሱና በምድር ላይ የሚርመሰመሱ ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ሕግ ይህ ነው። 47#ዘሌ. 10፥10።በዚህም በርኩስና በንጹሕ መካከል፥ በሚበላና በማይበላ ሕይወት ባለው ፍጥረት መካከል ለመለየት ነው።

ማድመቅ

ያጋሩ

ኮፒ

None

ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ