መጽሐፈ ኢያሱ 4:21-23

መጽሐፈ ኢያሱ 4:21-23 መቅካእኤ

ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ “በሚመጣው ዘመን ልጆቻችሁ አባቶቻቸውን፦ ‘እነዚህ ድንጋዮች ምንድን ናቸው?’ ብለው ሲጠይቁ፥ ለልጆቻችሁ እንዲህ ብላችሁ ታስታውቃላችሁ፦ ‘እስራኤል ይህን ዮርዳኖስን በደረቅ ምድር ላይ ተሻገረ፤’ እስክንሻገር ድረስ አምላካችሁ የኤርትራን ባሕር ከፊታችን እንዳደረቀ እንዲሁ እስክትሻገሩ ድረስ አምላካችሁ ጌታ የዮርዳኖስን ውኃ ከፊታችሁ አደረቀ።