መጽሐፈ ኢዮብ 29
29
1ኢዮብም ንግግሩን ቀጠለ፤ እንዲህም አለ፦
2“እግዚአብሔር ይጠብቀኝ እንደነበረው ጊዜ፥
እንደ ፊተኛው ወራት ምነው በሆንሁ!
3በራሴ ላይ መብራቱ በበራ ጊዜ፥
እኔም ጨለማውን አልፌ በብርሃኑ በሄድሁ ጊዜ፥
4ብርቱ እንደ ነበርኩበት ጊዜ፥
እግዚአብሔር ድንኳኔን ይጠብቅ በነበረበት ጊዜ፥
5ሁሉን የሚችል አምላክ ከእኔ ጋር ገና ሳለ፥
ልጆቼም በዙሪያዬ ሳሉ፥
6መንገዴ በቅቤ ይታጠብ በነበረ ጊዜ፥
ዓለቱ የዘይት ፈሳሽ ያፈስስልኝ በነበረ ጊዜ።
7ወደ ከተማይቱ በር በወጣሁ ጊዜ፥
በአደባባዩም ወንበሬን ባኖርሁ ጊዜ፥
8ወጣቶች እኔን አይተው ይሸሸጉ፥
ሽማግሌዎችም ተነሥተው ይቆሙ ነበር።
9መኮንኖች ከመናገር ዝም ይሉ፥
እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር።
10የታላላቅ ሰዎች ድምፅ ይደበቅ፥
ምላሳቸውም ከትናጋቸው ጋር ይጣጋ ነበር።
11የሰማችኝ ጆሮ ታሞግሰኝ፥
ያየችኝም ዐይን ትመሰክርልኝ ነበር፥
12የሚጮኸውን ችግረኛ፥
ወላጅ አልባውንና ረጂ የሌለውን አድኜ ነበርሁና።
13ለሞት የቀረበው ሰው በረከት በላዬ ይደርስ ነበር፥
የመበለቲቱንም ልብ እልል አሰኝ ነበር።
14ጽድቅን ለበስሁ እርሷም ለበሰችኝ፥
ፍርዴም እንደ ካባና እንደ ቆብ ነበረ።
15ለዐይነ ስውር ዐይን፥
መሄድ ለተሳነው እግር ነበርሁ።
16ለድሀው አባት ነበርሁ፥
ለማላውቀውም ሰው ጠበቃ ነበርሁ።
17የግፈኛውን መንጋጋ እሰብር፥
የነጠቀውንም ከጥርሱ ውስጥ አስጥል ነበር።
18እኔም፦ ‘በልጆቼ መካከል በክብር እሞታለሁ፥
ዕድሜዬንም እንደ አሸዋ አበዛለሁ፥’ እል ነበር፤
19ሥሬ በውኃ ላይ ተዘርግተው፥
ጠልም በቅርንጫፌ ላይ ያድር ነበር፤
20ክብሬ በእኔ ዘንድ ታድሶ፥
ቀስቴም በእጄ ውስጥ ለምልሞ ነበር።
21ሰዎች እኔን ሰምተው በትዕግሥት ተጠባበቁ፥
ምክሬንም ለማዳመጥ ዝም አሉ።
22ከቃሌ በኋላ አንዳች አልመለሱም፥
ንግግሬም በእነርሱ ላይ ተንጠባጠበ።
23ዝናብን እንደሚጠብቁ በትዕግሥት ጠበቁኝ፥
የበልግን ዝናብ እንደሚሹ አፋቸውን ከፈቱ።
24እነርሱ ባልታመኑ ጊዜ ሳቅሁላቸው፥
የፊቴም ብርሃን አበረታታቸው።
25መንገዳቸውን መረጥሁ፥
እንደ አለቃ ሆኜ ተቀመጥሁ፥
ንጉሥ በሠራዊቱ መካከል እንደሚኖር፥
ኀዘንተኞችን እንደሚያጽናና ኖርሁ።”
Currently Selected:
መጽሐፈ ኢዮብ 29: መቅካእኤ
ማድመቅ
ያጋሩ
ኮፒ
![None](/_next/image?url=https%3A%2F%2Fimageproxy.youversionapi.com%2F58%2Fhttps%3A%2F%2Fweb-assets.youversion.com%2Fapp-icons%2Fam.png&w=128&q=75)
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ