መጽሐፈ መሳፍንት መግቢያ
መግቢያ
መጽሐፈ መሳፍንት የእስራኤል ሕዝብ ወደ ከነዓን ከገቡበት ጊዜ አንሥቶ ንጉሣዊው መንግሥት እስከ ተመሠረተበት ጊዜ ድረስ ያለውን ታሪክ የያዘ ነው፤ ይህም ዘመን የእስራኤል ሕዝብ ጣዖትን በማምለክ በእግዚአብሔር ላይ ማመፅን ያበዙበት ጊዜ ነበር። ይህም ታሪክ የሚያመለክተው “መሳፍንት” የተባሉት ታላላቅ መሪዎች የፈጸሙአቸውን ተግባሮች ነው፤ ከእነዚህም መሳፍንት መካከል አብዛኞቹ የጦር መሪዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም በጣም የታወቀው ታላቅ መሪ፥ ሥራው ከምዕራፍ 13-16 ተዘርዝሮ የሚገኘው ሶምሶን የተባለው ሰው ነው።
ከመጽሐፉ የምናገኘው ታላቅ ትምህርት የእስራኤል ሕዝብ ህልውና የሚረጋገጠው ለእግዚአብሔር ባላቸው ታማኝነት ሲሆን፥ ለእርሱ ታማኞች ሳይሆኑ ሲቀሩ ዘወትር ጥፋት ይደርስባቸው እንደ ነበር የሚያስገነዝበው ነው፤ ከዚህም የበለጠ ሌላ ነገር አለ፤ ይኸውም ሕዝቡ ለእግዚአብሔር ያለውን ታማኝነት በማጓደሉ ጥፋት ቢደርስበትም እንኳ፥ ንስሓ ገብቶ ወደ እርሱ በተመለሰ ቊጥር እግዚአብሔር ያድነው ነበር።
አጠቃላይ የመጽሐፉ ይዘት
እስከ ኢያሱ ሞት ድረስ የነበረው ሁናቴ (1፥1—2፥10)
የእስራኤል መሳፍንት (2፥11—16፥31)
የተለያዩ ድርጊቶች (17፥1—21፥25)
ምዕራፍ
Currently Selected:
መጽሐፈ መሳፍንት መግቢያ: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ