እርሱም “ጠላታችሁን ሞዓብን ጌታ በእጃችሁ አሳልፎ ስለሰጣችሁ ተከተሉኝ” በማለት አዘዛቸው፤ እነርሱም ተከትለውት ወረዱ፤ ከዚያም ከዮርዳኖስ ወደ ሞዓብ የሚያሻግሩትን ስፍራዎች በመያዝ አንድም ሰው እንዳያልፍ ከለከሉ። በዚያን ጊዜ ብርቱና ይለኛ የሆኑ ዐሥር ሺህ ሞዓባውያንን ገደሉ፤ አንድም ሰውአላመለጠም። በዚያን ቀን ሞዓብ በእስራኤል ድል ሆነች፤ ምድሪቱም ለሰማንያ ዓመት ሰላም አገኘች። ከኤሁድ በኋላ ስድስት መቶ ፍልስጥኤማውያንን በበሬ መንጃ የገደለው የዓናት ልጅ ሻምጋር ተነሣ፤ እርሱም እንደዚሁ ደግሞ እስራኤልን አዳነ።
መጽሐፈ መሳፍንት 3 ያንብቡ
ያጋሩ
ሁሉንም ሥሪቶች ያነጻጽሩ: መጽሐፈ መሳፍንት 3:28-31
ጥቅሶችን ያስቀምጡ፣ ያለበይነመረብ ያንብቡ፣ አጫጭር የትምህርት ቪዲዮዎችን ይመልከቱ እና ሌሎችም!
ቤት
መጽሐፍ ቅዱስ
እቅዶች
ቪዲዮዎች