ትንቢተ ኢሳይያስ 13
13
በባቢሎን ላይ የተነገረ ትንቢት
1 #
ኢሳ. 47፥1-15፤ ኤር. 50፥1—51፥64። የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ስለ ባቢሎን ያየው ትንቢት፤ 2በተራቈተ ኰረብታ ዐናት ላይ ምልክት ስቀሉ፤ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ ጩኹ፤ በመሳፍንቱም በር እንዲገቡ፤ በእጅ ምልክት ስጡ። 3በድል አድራጊነቴ ደስ የሚላቸውን ቅዱሳኔን አዛለሁ፤ ቁጣዬንም እንዲፈጽሙ፤ ተዋጊዎቼን ጠርቻለሁ። 4በተራሮች ላይ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ፤ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ! በመንግሥታትም መካከል፤ እንደ ተጨናነቀ ሕዝብ ድምፅ የሆነውን ውካታ ስሙ! የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሠራዊቱን ለጦርነት አሰልፎአል። 5ጌታና የቁጣው ጦር መሣሪያ፤ ምድሪቱን በሙሉ ለማጥፋት፤ ከሩቅ አገር፤ ከሰማያትም ዳርቻ መጥተዋል። 6#ኢዮብ 1፥15።የጌታ ቀን ቀርቦአልና አልቅሱ፤ ሁሉን ቻይ ከሆነ አምላክ ቀኑ እንደ ጥፋት ይመጣል። 7ስለዚህ እጆች ሁሉ ሽባ ይሆናሉ፤ የሰውም ሁሉ ልብ ይቀልጣል። 8ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል። 9እነሆ፤ የእግዚአብሔር ቀን ጨካኝ ነው፤ ምድርን ባድማ ሊያደርጋት፤ በውስጧም ያሉትን ኀጢአተኞች ሊያጠፋ፤ ከመዓትና ከብርቱ ቁጣ ጋር ይመጣል። 10#ሕዝ. 32፥7፤ ማቴ. 24፥29፤ ማር. 13፥24-25፤ ሉቃ. 21፥25፤ ራእ. 6፥12፤13፤ 8፥12።የሰማይ ከዋክብትና ሠራዊታቸው፤ ብርሃን አይሰጡም፤ ፀሓይ ገና ከመውጣቷ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም። 11ዓለምን ስለ ክፋቷ፤ ክፉዎችንም ስለ ኀጢአታቸው እቀጣለሁ፤ የትዕቢተኞችን እብሪት እሽራለሁ፤ የጨካኞችንም ጉራ አዋርዳለሁ። 12ሰውን ከነጠረ ወርቅ ይልቅ ውድ፤ ከኦፊርም ወርቅ ይበልጥ ብርቅ አደርጋለሁ። 13ስለዚህ በሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መዓት፤ ቁጣው በሚነድበት ቀን፤ ሰማያትን እነቀንቃለሁ፤ ምድርንም ከስፍራዋ አናውጣለሁ። 14እንደሚታደን ሚዳቋ፤ እረኛም እንደሌለው የበግ መንጋ፤ እያንዳንዱ ወደ ወገኑ ይመለሳል፤ እያንዳንዱም ወደ አገሩ ይሸሻል። 15የተማረከ ሁሉ ይወጋል፤ የተያዘም ሁሉ በሰይፍ ይወድቃል። 16ዐይናቸው እያየ ሕፃናታቸው ይጨፈጨፋሉ፤ ቤታቸው ይዘረፋል፤ ሚስቶቻቸው ይደፈራሉ። 17እነሆ፤ ለብር ደንታ የሌላቸውን፤ በወርቅም ደስ የማይሰኙትን፤ ሜዶናውያንን አስነሣባቸዋለሁ። 18ቀስታቸው ጐበዞችን ይፈጃል፤ ሕፃናትን አይምሩም፤ ዐይናቸውም ለልጆች አይራራም። 19#ዘፍ. 19፥24።የመንግሥታት ዕንቁ፤ የከለዳውያን ትምክሕት፤ የሆነችውን ባቢሎንን፤ እግዚአብሔር እንደ ሰዶምና እንደ ገሞራ ይገለብጣታል። 20በዘመናት ሁሉ የሚቀመጥባት አይኖርም፤ የሚቀመጥባትም የለም ዐረብ በዚያ ድንኳኑን አይተክልም፤ እረኛም መንጋውን በዚያ አያሳርፍም። 21#ኢሳ. 34፥14፤ ሶፎ. 2፥14፤ ራእ. 18፥2።ነገር ግን የምድረ በዳ አራዊት በዚያ ይተኛሉ፤ ቀበሮዎች ቤቶቿን ይሞላሉ፤ ጉጉቶቿ በዚያ ይኖራሉ፤ በበረሓ ፍየል የሚመሰሉ አጋንንትም ይዛለሉበታል። 22ተኩላዎችም በግንቦቻቸው፥ ቀበሮዎችም በተዋቡ ቤተ መንግሥቶቿ ይጮኻሉ፤ ጊዜዋ ቀርቦአል፤ ቀኗም አይራዘምም።
Currently Selected:
ትንቢተ ኢሳይያስ 13: መቅካእኤ
ማድመቅ
Share
Copy
ያደመቋቸው ምንባቦች በሁሉም መሣሪያዎችዎ ላይ እንዲቀመጡ ይፈልጋሉ? ይመዝገቡ ወይም ይግቡ