ኦሪት ዘፍጥረት 9:1-11

ኦሪት ዘፍጥረት 9:1-11 መቅካእኤ

እግዚአብሔርም ኖኅንና ልጆቹን ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ “ብዙ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት። እንስሶች፥ ወፎች፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና ዓሣዎች ሁሉ እናንተን በመፍራትና በመደንገጥ ይኑሩ፤ ሁሉም በሥልጣናችሁ ሥር ይሁኑ። ከዚህ በፊት የአትክልት ዓይነቶችን ምግብ አድርጌ እንደሰጠኋችሁ እነዚህንም ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች ሁሉ ምግብ እንዲሆኑአችሁ ሰጥቻችኋለሁ። ነገር ግን ደም ያለችበትን ሥጋ አትብሉ፥ ምክንያቱም በደም ውስጥ ሕይወት አለ። ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፥ ከአራዊት እና ከሰውም ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ። ሰው የተፈጠረው በእግዚአብሔር አምሳያ ስለ ሆነ፥ ሰውን የሚገድል ሁሉ በሰው እጅ ይሞታል። እናንተ ፍሬያማ ሆናችሁ ተባዙ፤ ዘራችሁ በምድር ላይ ይብዛ።” ከዚህ በኋላ እግዚአብሔርም ለኖኅ፥ ከእርሱም ጋር ለልጆቹ እንዲህ ብሎ ተናገረ፦ “እነሆ፥ እኔም ቃል ኪዳኔን ከእናንተ ጋር፥ ከእናንተም በኋላ ከዘራችሁ ጋር እመሠርታለሁ፤ ይህም ከእናንተ ጋር ላሉትም ሕያው ነፍስ ላላቸው ሁሉ፥ ከእናንተ ጋር ከመርከብ ለወጡት አእዋፍ፥ ለእንስሳትም፥ ለምድር አራዊትም ሁሉ፥ ለየትኛውም የምድር አራዊት ሁሉ ይሆናል። ቃል ኪዳኔንም ለእናንተ እመሰርታለሁ፥ ሕያው ፍጥረት ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውኃ አይጠፉም፥ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውኃ አይመጣም።”

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}