ኦሪት ዘፀአት 31:12-15

ኦሪት ዘፀአት 31:12-15 መቅካእኤ

ጌታ ሙሴን እንዲህ አለው፦ “አንተ ግን ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሰንበቶቼን ፈጽሞ ጠብቁ፥ ይህ የምቀድሳችሁ ጌታ እኔ እንደሆንሁ እንድታውቁ በእኔና በእናንተ መካከል ለትውልዶቻችሁ ምልክት ነውና። ስለዚህ ለእናንተ ቅዱስ ነውና ሰንበትን ጠብቁ፤ የሚያረክሰው ፈጽሞ ይገደል፥ በእርሷ ሥራን የሚሠራ ሁሉ ከሕዝቡ መካከል ተለይቶ ይጥፋ። ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፥ ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ የተቀደሰ የዕረፍት ሰንበት ነው፤ በሰንበት ቀን የሚሠራ ሁሉ ፈጽሞ ይገደል።

ቪዲዮ ለ {{ዋቢ_ሰዉ}}